ከግሪክ የተላኩ የፓኬት ቦምቦችና ያስከተሉት ስጋት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ከግሪክ የተላኩ የፓኬት ቦምቦችና ያስከተሉት ስጋት

ለጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የተላከ አንድ ፈንጂ የያዘ ፓኬት ትናንት በመራሄ መንግስቱ ጽህፈት ቤት ከደረሰ በኋላ ማምከን መቻሉ ታውቋል።

default

የጀርመን ሀገር አስተዳደር ሚንስትር ቶማስ ደ ሜዝየር እንደገለጹት፡ ፓኬቱ የመጣው ከግሪክ ነው። ለኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ የተላከ ፈንጂ የያዘ አንድ ሌላ ፓኬት ደግሞ የኢጣልያ ፈንጂ አምካኞች እጅ ቢቀጣጠልም፡ ጉዳት አለማድረሱ ተሰምቶዋል። ለፓኬቶቹ ቦምቦች የግሪክ የግራ አክራሪዎች ተጠያቂ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተጠርጥሮዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic