ከዓለም የሳቅ ንጉሥ ጋር - በሳቅ | ባህል | DW | 29.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ከዓለም የሳቅ ንጉሥ ጋር - በሳቅ

ለመጀመርያ ጊዜ ለሳቅ ዉድድር ጀርመን ሀገር እንደመጣ የሚናገረዉ ለዓለም የሳቅ ንጉሱ ለበላቸዉ ግርማ፤ ሳቅ ፍቅር ነዉ፤ ሳቅ መላ አካላትን የሚያንቀሳቅስ ስፖርት ነዉ፤ ሳቅ ሰላምን መፍጠርያ መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ጤና ነዉ፤ ሳቅ ደስታ ነዉ፤ ሳቅ ሕይወት ነዉ፤ ሳቅ የሰላም መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ የፍቅር መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ወጣት የሚያደርግ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 14:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
14:28 ደቂቃ

ከሳቅ ንጉሥ ጋር - በሳቅ

ሳቅ ዉበትን ጤንነትን የሚያመጣ ነዉ፤ እድሜን የሚያድስ ነዉ፣ ሳቅ ማኅበራዊ ግንኙነትን አንድ የሚያደርግ ነዉ። ሳቅ ዓለማቀፋዊ ቋንቋ ነዉ። ሳቅ በግል ሕይወትና በማኅበራዊ ሕይወት መካከል ያለዉን ሽብር የሚያቆም፤ የሚያቀዘቅዝ ነዉ። ሰዉ ከሳቀ ደሃ አይደለም ይላሉ ፈረንጆች፤ በሀገራችንም ከፍትፍቱ ፊቱ ነዉና፤ ሳቅ ከምግብ የሚበልጥ ነዉ። ሳቅ ከፈጣሪ እንደምንተነፍሰዉ አየር በነፃ ለሰዉ ልጆች ሁሉ የታደለ ፀጋ ነዉ፤ ሲል ለሳቅ ያለዉን ፍቺ ይተነትናል። በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የሣቅ ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ላይ የከፈተዉ የዓለም የሳቅ ንጉስ በላቸዉ ግርማ፣ በሳቅ በተወዳደረበት መድረክ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ የመጀመርያዉ ትልቁ ዉጤት መሆኑን ገልፆአል። በቅጣዩ ዉድድሩ ደግሞ የሳቅ ሰዓቱን በ2፡14 ደቂቃ በማስረዘም ብቸኛዉ ያለም የረጅም ሰዓት ሳቅ ባለቤት ሆነ። በዚህም “ወርልድ ማስተር ላፍተር (world laughter master)” የሚለዉን ስም ተሰቶታል። impossible challenge በሚል ዉድድር ላይ ተወዳድሬ አዋርድ ተሸላሚ መሆንዋል። ይህ ሽልማቱ በብሔራዊ ሙዚየም መቀመጡን ይናገራል። ከሳቁ ሌላ ዓለማቀፍ የሳቅ ንጉስ እንደተባለም በዚህ መጠርያዉ ብቻ መጠራትን እንደሚሻ የ 50 ዓመቱ በላቸዉ ግርማ ይናገራል። ዛሬ የዓለም የሳቅ ንጉሱ በላቸዉ ግርማ ከ 3 ሰዓት ተኩል በላይ መሳቅ መቻሉ ጀርመን ላይ ተመዝግቦለታል። በላቸዉ ግርማ በዚሁ በሳቁ የተለያዩ ዓለም ሃገሮችን ዞርዋል። እንደዉም በትምህርት ቤቶች የህክምና ጣብያዎች እየሄደ ሳቅ ለጤንነት ያለዉን ከፍተኛ ድርሻ እየተናገረ በሳቅ ፍርስ እያደረገ የሥነ-ልቦና ድጋፍ እንደሚሰጥ ነዉ የገለፀዉ። ሰሞኑን ጀርመን ሀገር ላይ በተደረገዉ የሳቅ ዉድድር ላይ ተካፍሎ ለረጅም ሰዓታት መሳቅ መቻሉን ፤ በዓለም አንደኛ መሆኑን አስመስክሮና ምስክር ወረቀቱን ይዞ ወደ ሀገሩ ተመልሶአል። ከሳቅ ንጉሱ ከበላቸዉ ግርማ ጋር ያደረግነዉን ሙሉ ዉይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበAudios and videos on the topic