ከዉጭ መልስ ንግድ | ኤኮኖሚ | DW | 03.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ከዉጭ መልስ ንግድ

ብዙዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ይወጣሉ፤ ይሰደዳሉ። እንዳወጣጣቸዉ ሰንቀዉ የሚነሱት ዓላማና ህልም እንደመለያየቱ፤ ያለሙትን የጨበጡ፤ የተመኙትን ያገኙም ብዙ አይሆኑም።

የሄዱበት ሀገር አዲስ ባህልና አኗኗር የህይወት አቅጣጫቸዉን በበጎ የቀየረላቸዉ የመኖራቸዉን ያህል፤ ያልጠበቁት የገጠማቸዉ፤ ያም ከማይላቀቁት አዙሪት ከቶ፤ ቆይ ዘንድሮ፤ ቆይ የሚመጣዉ ዓመት እያሉ ጥሪት ለመቋጠር ሲዋትቱ ዓመት ዓመትን እያፈራረቀ፤ እነሱም ወደተመኙት ሳይደርሱ ጊዜዉ የነጎደባቸዉ ጥቂት አይደሉም። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ ከእነዚህ ይለያሉ፤ ከሄድኩበት ሀገር ገንዘብ ቢቀር ጠንካራ የሥራ መንፈስን ሰንቄ በመመለስ የራሴን እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ባይ ናቸዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic