1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከእገታ የተለቀቁት ተማሪዎች የት ናቸው?

ዓርብ፣ ጥር 8 2012

ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/3WMkc
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

ከእገታ የተለቀቁት ከወላጆቻቸው ያልተገናኙት የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ነዉ

ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ። ተማሪዎቹ ከእገታ ከተለቀቁ በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአካባቢው የስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ዛሬ ተናግረዋል።
የታገቱ ቀሪ ስድስት ተማሪዎችን ለማስለቀቅም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው ባልቻ ጋር የስልክ ቃለ-ምልልሱን ያደረገው ታምራት ዲንሳ ነው። ተማሪዎቹ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መኖራቸውን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው ስልክ ብንደውልም ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ