ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አቶ ማሞ ምኅረቱ "ገንዘብ የማተምና የማሠራጨት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ማስተዳደር፣ የገንዘብ ፖሊሲ የማውጣትና የመተግበር" ኃላፊነት የተሰጠውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገዥነት ሲመሩ በርካታ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል። የዋጋ ንረትና የውጭ ምንዛሪ እጥረት የባንኩና የገዥውን መፍትሔ ከሚሹ መካከል ናቸው። ስለ ሹመታቸው ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የ2016ን በጀት ሲያዘጋጁ "ከውጭ ሊገኝ የሚችልን ዕርዳታ እና ብድር በማሰብ" ሊሆን እንደማይገባ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ አሳስበዋል። የፕሪቶሪያ የሰላም ሥምምነት እና የሽግግር ፍትኅ አተገባበር ምዕራባውያን የከለከሉትን እርዳታ እና ብድር ለመፍቀድ ቅድመ-ሁኔታ አድርገዋል።
በትይዩ ገበያው የዶላር የምንዛሪ ተመን በከፍተኛ መጠን ሲያሻቅብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "በሕገ-ወጥ የሐዋላ ሥራ" የጠረጠራቸውን ከ390 በላይ ግለሰቦች የባንክ አካውንት ማገዱን ገልጿል። ባለሙያዎችና የግብይቱ ተሳታፊዎች እንደሚሉት ቻይና በትይዩ ገበያ የሚዘዋወረው ገንዘብ መዳረሻ ስትሆን በዱባይ የሚገኙ ነጋዴዎች ተመኑን የመወሰን ጉልበት አላቸው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ዝውውርን ጠበቅ የሚያደርግ መመሪያ በሥራ ላይ አውሏል። መመሪያው የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የዋጋ ግሽበትና የበጀት ጉድለት በበረታበት ወቅት ገቢራዊ የሆነ ነው። ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ መመሪያው መንግሥት "አሉ በሚባሉ ቀዳዳዎች በሞላ የውጭ ምንዛሪ ገቢውን ለመጨመር" ያደረገው ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።