ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔተ ቬበር ከኢትዮጵያ "መንግሥት በኩል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር ምልክት ከሰጠ ወይም ካስጀመረ ህወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በመቐለ ጉብኝታችን ተረድቻለሁ" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ቬበር እንደሚሉት ለድርድር "የመተማመን እጦት ዋና እንቅፋት" ነው።
የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፈጣሪ ምስጋና እንዲቀርብ ጥሪ የሚያቀርብ ዘለግ ያለ ደብዳቤ የተደበላለቀ ምላሽ አግኝቷል። በጥሪው ተስማምተው «አሜን» ያሉ የመኖራቸውን ያክል ሐይማኖት እና ፖለቲካ መደበላለቁ ያሳሰባቸው፤ አገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ያልተጣጣመላቸው ትችት ጽፈዋል። የአል ሸባብ ጥቃት እና የደራርቱ ቱሉ ጥሪም ውይይት ፈጥረዋል።
"እኛ እንደተገነዘብነው መንግሥት እስካሁን ለድርድሩ ያስቀመጠው ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የለም፤ሆኖም ከመቀሌው ጉብኝታችን እንደተረዳሁት ከሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ በኩል በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ የቀረበ ቅድመ ሁኔታ አለ።" :ዶ/ር አኔተ ቬበር
“ኢትዮጵያዊ ሀገሩ የት ነው?” ሳነብ ዉስጤ የሆነ ነገር መረበሽ እየተሰማኝ ነበር። የመደበላለቅ ስሜት። አንቺ ቀበጥ ሃገርሽ ላይ ሆነሽ ምን ልሁን ነዉ የምትይዉ? ብለሽኝ ይሆናል። የሆነ ነገር ረብሾሽ፤ ጩሂ ጩሂ ብሎሽ አያዉቅም? ከሃገራቸዉ ተሰደዉ ሆድ ለባሳቸዉ አንቺ ጻፍሽላቸዉ። ሃገራችን ላይ ሆነን መጠግያ ላጣንስ? አንድ ወገን ለሌለንስ?