ከኢኮኖሚዉ አለም | ኤኮኖሚ | DW | 10.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ከኢኮኖሚዉ አለም

የምጣኔ ሐብቱ ድቀት ቀድሞ የነዘራትም የአለም የምጣኔ ሐብት ዋና መዘዉሯን ዩናይትድ ስቴትስን ነዉ።

default

የመኪና አምራቾቹ ኪሳራ

ከዩናይትድ ስቴትስ ጀምሮ-አለምን ያዳረሰዉ የገንዘብ ቀዉስ፥ በባንኮች እና በኢንሹራን ኩባንዮች አጉዞ ከአጠቃላይ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት ላይ ደርሷል።የምጣኔ ሐብቱ ድቀት ቀድሞ የነዘራትም የአለም የምጣኔ ሐብት ዋና መዘዉሯን ዩናይትድ ስቴትስን ነዉ።ኪሳራዉ ከሌሎቹ ይልቅ በሰወስቱ ግዙፍ የመኪና ኩባኖዮች ላይ ከፍቶ መንግሥት የመድን ድጎማ እንዲሰጣቸዉ እየተማፀኑ ነዉ። ጥያቄዉ የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ የአሜሪካ ፖለቲከኞችንና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎችን እሁለት ከፍሎ እያወዛገበ ነዉ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ፖዝን-ፖላንድ ላይ ያስተናገደዉን የተፈጥሮ ጥበቃ ጉባኤ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደሚለዉ በኢንዱስትሪ የገፋዉ አለም ከገጠመዉ የምጣኔ ሐብት ኪሳራ የሚወጣበት መንገድ በሚያሰላስልበት ወቅት አሁን-የተፈጥሮ ሐብትን ለማስከበር ብዙ ትኩረት መስጠቱ፥ ገንዘብ ማዉጣቱም ብዙ አጠራጥሯል።