1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 76 በመቶው የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም ተገለጸ

ሐና ደምሴ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 16 2017

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 76% ኔትወርክ ባለበት አካባቢ ቢኖርም አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም የግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል ኮምዩንኬሽንስ ማኅበር ጥናት ይፋ አደረገ። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ክፈቱትን ለመቀነስ መሠረተ-ልማት ማስፋፋትን ጨምሮ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/4mGW4
ኢትዮጵያ የሞባይል ተጠቃሚዎች
ከኢትዮጵያ ሕዝብ 76% ኔትወርክ ባለበት አካባቢ ቢኖርም አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም የግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል ኮምዩንኬሽንስ ማኅበር ጥናት ይፋ አደረገ።ምስል DW/J. Jeffrey

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 76 በመቶው የሞባይል ኢንተርኔት እንደማይጠቀም ተገለጸ

በኢንተርኔት አገልግሎት ሽፋን ውስጥ ከሚገኙት የቴሌኮም ተጠቃሚዎች መካከል 24% የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ብቻ የኔት ዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው ተባለ።

ከኢትዮጵያ ህዝብ 76% የሚሆነው ምንም እንኳን ኢንተርኔት አገልግሎት ያለበት አካባቢ ቢኖርም አሁንም በኔትዎርክ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት እንደማይጠቀም ግሎባል ሲስተም ፎር ሞባይል ኮምንኬሽን  አሶሲየሽን  (GSMA) ባወጣው ሪፓርት ገልጿል

ጂ.ኤስ.ኤም ኤ  ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን  ሪፖርት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ  ከ  4 አመት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2028 ኢትዮጵያ ከሚኖራት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ አስተዋጽዖ ያደርጋል ብሏል።

«በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»

 የኢትዮ ቲሌ ቴሌኮም በዲጂታል ሽግግር ላይ ትኩረት   በማድረግ  በዲጂታል ቴክኖሎጂ  ዘርፍ  ያደረጋቸውን ማሻሻያ  እና እድገት የጠቆመው ሪፖርት  ካንፓኒው  በፈረንጆቹ 2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ሥራዎች  ይፈጥራል  ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የኩባንያቸው ከ45 ሚሊዮን በላይ የኩባንያቸው ደንበኞች ኢንተርኔት እንደሚጠቀሙ ገልጸው ክፈቱትን ለመቀነስ መሠረተ-ልማት ማስፋፋትን ጨምሮ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል። ምስል Michael Tewelde/Xinhua/picture alliance

ኢትዮጵያን ዲጂታል የማድረግ ውጥን፡ ኢትዮ ቴሌኮም

አሁን እስካለንበት የፈረንጆቹ 2024 ድረስ ከ90 ሚሊዮን በላይ የተንቀሳቃሽ  የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች  በሀገሪቱ እንዳሉ የተነገር ቢሆንም አሁንም  ከፍተኛ የአጠቃቀም ክፍተት እንዳለ የጠቆመው ሪፓርት ምንም እንኩዋን ፣ በኔትወርክ ሽፋን  ቢኖርም  76 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም የሞባይል ኢንተርኔት እይጠቀምም ሲል ሪፖርቱ አትቷዋል ፡፡

DW ያነጋገራቸው አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሞባይል ስልክ ቢኖረኝ እጅ ስልኬ የኢንተርኔት ተጥዕቃሚ አይደለሁም ሲሉ ይናገራሉ።

በስልኮቻችን የሚገኙ ግላዊ መረጃዎቻችን ከመንታፊዎች እንዴት እንከላከል?

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራስኪያጅ ፍሪህይወት ታምሩ  ባለፉት ጥቂት አመታት ያሳየነው የ መሰረተ ልማት እድገት እና ፈጣን እንቅስቃሴ ይህንንኑ ክፍተት ለመሙላት ነው ሲሉ በያመቱ የተጠቃሚው ቁጥር መጨመር ምስክር ነው ብለዋል

በኢትዮጵያ ሁሉም   የመንግስት አገልግሎት ክፍያዎች በሙሉ  በቴሌብር ብቻ  እንዲሆኑ መደረጉ ይታወቃል።

ሐና ደምሴ

እሸቴ በቀለ