ከኢሬቻ እልቂት በኋላ የተባባሰዉ ተቃዉሞ  | ፖለቲካ | DW | 04.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢሬቻ እልቂት በኋላ የተባባሰዉ ተቃዉሞ 

ከኢሬቻ እልቂት በኋላ የተባባሰዉ ተቃዉሞ 

በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ በነበረዉ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በታዳሚዎቹና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተፈጠረዉ ግጭት የብዙ ሰዉ ሕይወት ማለፉ እየተዘገበ ነዉ። ይህንን ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃዉሞ መባባሱንና አሁንም የሰዉ ሕይወት እየጠፋ ነው ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:17 ደቂቃ

ተባብሶ የቀጠለዉ ተቃዉሞ

ንብረቶች መዉደማቸዉና ወጣቶች በርካታ መሰርያን ከፖሊሶች መንጠቃቸዉ ያነጋገርናቸዉ የዓይን እማኞች ገልፀዉልናል። በአከባብያችሁ ያለዉ ሁኔታ ምን ይመስለል? ብለን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዓይን እማኞችን ጠይቀን ነበር። 
በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ በነበረዉ ዓመታዊዉ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የመንግስት የፀጥታ ሃይል በታዳሚዎቹ ላይ በወሰዱት ርምጃ የብዙ ሰዉ ሕይወት ማለፉ እየተዘገበ ይገኛል። ይህንንም ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ተቃዉሞ መባባሱንና አሁንም ሰዉ እየሞተ መሆኑን በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የምኖሩት ነዋርዎች ይናገራሉ።
የአዳማ ነዋሪ የሆኑት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁት የኢሬቻ በዓል ታዳሚ እንደነበሩና የታዘቡት ክስተት እንዳሳዘናቸዉና በእሁድ እለት ምሽት ላይ ከቢሾፊቱ 10 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘዉ ዱከም ከተማ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ የሰዉ ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። 
በደምቢ ዶሎ ከተማ 04 ቀበሌ ነዋር ነኝ ያሉትን ግለሰብ በበኩላቸዉ የኢሬቻ ክስተትን ተከትሎ በትላንትናዉ እለት በከተማዋ ህዝብ ተቃዉሞ ስያሰማ እንደነበር ተነግረዉ፣ የፀጥታ ኃይላት እንዴት ተኩስ እንደከፈቱ እና ሰዎች እንደሞቱ እንዲህ ገልፀዉልናል። 
«በትላንትናዉ እለት የመንግስት ሰራተኞች እንዲገቡ ተደረገ። ሱቅ ከፍተዉ የነበሩትም እንዲዘጉ ታዘዙ። ከዛ በኋላ ተኩስ ከፈቱ። በዚህም ምክንያት የተጎዱ  ብዙ ልጆች አሉ። እኔ የማዉቀዉ ሁለት ሰዉ መሞቱን ነዉ። አንዱም ቢቂላ ሂካ ስባል፣ የአዶ-ሳኮ ነዋሪ ነበር፤የቀብር ሥነ-ስረዓቱ ዛሬ ይፈፀማል። ሌላኛዉ ሟች ደግሞ ኦብሳ ይባላል። በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ አራት ሰዉ መሆኑ ነዉ። አስክሬን ለማንሳት የሞከሩትም በጥይት ተመተዋል።»
በዛሬዉም እለት የፀጥታ ኃይሎች በየቤቱ እየሄዱ ሽማግሌንና አሮጊቶችን መንገድ ላይ አዉጥቶ መንገድ ለመዝጋት ተቃዋምዎች የተጠቀሙትን ድንጋይ እንድያነሱ እየተደረጉ መሆናቸዉን ይናገራሉ። 
በደቡብ ኦሮሚያ የምትገኘዉ የቡሌ ሆራ ከተማም ከፍተኛ ተቃዉሞ እንደነበረ እንዲሁም ሰዎች መሞታቸዉንና የመንግስት ተቃዋማትና ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸዉን የአከባቢዉ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ እንዲህ ገልፀዋል።
«በቡሌ ሆራ አከባቢ ከጥዋቱ ጀምሮ አንድም ቢሮ ሳይቀር፣ ፍርድ ቤት፣ የከተማዉ መስተዳደር፣ መኪናዎችንና ሁለት እስር ቤቶች እስረኞች ከወጡ በዋላ ተቃጥለዋል። ወጣቶችም ከፖሊሶችና የሰላም አስከባሪ ከሚባሉት ብዙ መጠመንጃዎች ከወሰዱ በኋላ ቤታቸዉንም አቃጥለዋል። የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ትላንትም ዛሬም ዝግ ናቸዉ። አሁን ከቡሌ ሆራ 17 ኪሎሜትር ርቃ ከምተገኘዉ ጋርባ ተብላ በምትጠራዉ አከባቢ ልዩ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ ሁለት ሰዉ ሲሞት ስድስት ሰዉ ደግሞ ቆስለዋል።»
በዚሁ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ ደህረ-ገፃችን ላይ እንድወያዩ ከጋብዝናቸዉ ዉስጥ አንዳንዶቹ ፖሊስ በወሰደዉ ርምጃ ማዕረግ ሊሰጣቸዉ ይገባል ሲሉ ሌሎች ደግሞ «ወያኔ ሆን በሎ መሰርያ ባይተኩስ ህዝብ አይረበሽም፣ እሺ አስለስቃሽ ጢስ መተኮስስ ለምን አስፍለገ? እኔ እንደ ሚመስለኝ ከሆነ ወያኔ ሆን ብሎ ያደረገዉ ነገር ነዉ፣» ሲሉ መንግስትን ተችተዋል።
በመንግስት በኩል በክልሉ ያለዉን መረጃ ለመዉሰድ ስንል ያደረገነዉ ሙከራ አልተሳካም።
መርጋ ዮናስ 
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች