ከ«ኢሕአዴግ» ወደ «ብልጽግና»? | ኢትዮጵያ | DW | 25.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከ«ኢሕአዴግ» ወደ «ብልጽግና»?

ኢሕአዴግ ከእለት ተእለት ፖለቲካዊ አውድ ገሸሽ ሊደረግ፤ አለያም ሊወገድ ጠርዝ ላይ ተጠግቷል። ለምን ያኽል ጊዜ እንደሚቆይ ባይታወቅም በምትኩ «ብልጽግና» የተሰኘ አዲስ ፓርቲ የፖለቲካ መድረኩን ሊቆጣጠር ዳር ዳር እያለ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 29:58

የኢሕአዴግ ውሕደት ጸድቋል፤ የሕወሓት እጣ ፈንታስ?

ኢሕአዴግ ከእለት ተእለት ፖለቲካዊ አውድ ገሸሽ ሊደረግ፤ አለያም ሊወገድ ጠርዝ ላይ ተጠግቷል። ለምን ያኽል ጊዜ እንደሚቆይ ባይታወቅም በምትኩ «ብልጽግና» የተሰኘ አዲስ ፓርቲ የፖለቲካ መድረኩን ሊቆጣጠር ዳር ዳር እያለ ነው። ኢሕአዲግ ከእንግዲህ ኢሕአዲግነቴ አክትሞ «የኢትዮጵያውያን ብልጽግና ፓርቲ» በአጭሩ «ብልጽግና» ነው የምትሉኝ ያለበት የፓርቲው ነው የተባለ መተዳደሪያ ደንብ በኢንተርኔቱ ዓለም ተሰራጭቷል።

ኢሕአዲግ ወደ አዲሱ ፓርቲ የሚሸጋገረው በግንባርነት አባል የነበሩትን እና እስካሁን አጋር ፓርቲ የተሰኙ የክልል ፓርቲዎችን በማካተት እንደሚኾን ገልጧል። ከግንባሩ አባላት አራት ፓርቲዎች ግን የኢሕአዲግ የራሱ ዋና መሥራች የነበረው ሕወሓት የግንባሩ ውሕደትን እንደማይቀበል በኢሕአዴግ የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ወቅት ገልጧል። ውሕደቱ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ሐሙስ ኅዳር 11 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ሲጸድቅም ሕወሓት አልተገኘም። የአዲሱ ውሑድ ፓርቲ ሕገ-ደንብ በበነጋታው ዓርብ ዕለት ከሕወሓት ውጪ ሌሎች አባላት በተገኙበት በ«ሙሉ ድምጽ» መጽደቁ ተገልጧል።

የውሕደት ሒደቱ በሕወሓት እና በሌሎች አንዳንድ የሀገሪቱ ፓርቲዎች መካከል ተቃውሞ ደርሶበታል። የኢሕአዲግ የውሕደት ሒደት ከመጨረሻ ግቡ ደርሶ ውሕዱ ፓርቲ በይፋ የሚታወጅ ከኾነ በሀገሪቱ ወደፊት የሚኖረው እድል እና ተግዳሮት ምንድን ነው? የውሕደቱ ሒደትስ ምን ይመስላል?

ሙሉ ውይይቱን፦ ከድምፅ ማዕቀፉ ማድመጥ ይቻላል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ 

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች