ከአገር ጋር ትዉዉቅ | ባህል | DW | 22.04.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ከአገር ጋር ትዉዉቅ

የለቱ የባህል ጥንቅር በትዉልድ ኢትዮጽያዊ ግን በጀርመን አገር አድጎ በቅርቡ አገሩ ኢትዮጽያን የተዋወቀ ወንድም በመድረኩ ጋብዟል። ኢትዮጽያን ለማወቅ ባደረገዉ ጉጉት ብቻ ቋንቋዉን ተምሮ፤ መጻፍ ማንበብም ችሎአል።

default

ትዉዉቅ

የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርቱን በማስትሪት ዲግሪ ለማጠናቀቅ በዝግጅት ላይ ያለዉ ወጣት የማስትሪት መመረቅያ ስራዉን በኢትዮጽያ ባህል ዙርያ እንዲሁም በአፍሪቃዉ ቀንድ ያለዉን ሁኔታ በጽሁፍ በማስፈር ላይ ይገኛል። ወጣቱ አፉን ከፈታበት ከጀርመንኛ ቋንቋ ሌላ እንግሊዘኛ ፈረንሳይኛ አማርኛ ቋንቋን ይናገራል በመቀጠል የኢትዮጽያን ቋንቋዎች በተለይም ኦሮምኛ እና ትግርኛን ለማቀዉ በጥረት ላይ ነዉ። የዕለቱ የባህል መሰናዶ እንደተለመደዉ በጀርመን ድረ-ገጾች እና ጋዜጦች ሰሞኑን ምን ባህል ጠቀስ ነገሮች ሰፈሩ በማለት ይጀምራል ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ