ከታንዛንያ እስር ቤቶች ከ1900 በላይ ኢትዮጵያውያን ሊለቀቁ ነዉ | አፍሪቃ | DW | 07.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ከታንዛንያ እስር ቤቶች ከ1900 በላይ ኢትዮጵያውያን ሊለቀቁ ነዉ

በታንዛንያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታንዛኒያ መንግስት ከ1900 በላይ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ለመፍታት መወሰኑን ገለፀ። ኤምባሲዉ በፌስቡክ ገፁ ባሰራጨዉ መረጃ በታንዛኒያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን በተመለከተ ከአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ከፓርላማው አፈ-ጉባኤ እና ከዛንዚባር ፕሬዝዳንት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ማድረጉን ገልፆአል።

በታንዛንያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታንዛኒያ መንግስት ከ1900 በላይ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ለመፍታት መወሰኑን ገለፀ። ኤምባሲዉ በፊስቡክ ገፁ ባሰራጨዉ መረጃ በታንዛኒያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን በተመለከተ ከአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ከፓርላማው አፈ-ጉባኤ እና ከዛንዚባር ፕሬዝዳንት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ማድረጉን ገልፆአል።  በውይይቱ ጉዳዩ በከፍተኛ አመራሩ ውሳኔ እንዲሰጥበት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸው እንደነበረና፤ በዛሬው እላት ከታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  Augustine Mahiga በጽ/ቤታቸው በተደረገ ውይይት በተለያዩ የታንዛኒያ እስርቤቶች የሚገኙ ከ1900 በላይ ኢትዮጵያውያንን ሙሉ በሙሉ በምህረት ለመልቀቅ የታንዛኒያ መንግስት የፖለቲካዊ ውሳኔ ማስተላለፉን ለኤንባሲዉ መረጃ እንደደረሰዉ አስታዉቋል። እስረኞቹን የማስፈታት እና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ስራ በቀጣይ በሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች የሚጀመር ይሆናልም ብሎአል ኤምባሲዉ።

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ