ከብ/ቡድኗ ድል በኋላ የጀርመን ገጽታ በሌሎች እይታ | ስፖርት | DW | 17.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

ከብ/ቡድኗ ድል በኋላ የጀርመን ገጽታ በሌሎች እይታ

ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ በፍጻሜ ግጥሚያ ጀርመን አርጀንቲናን አንድ ለባዶ አሸንፋ ለአራተኛ ጊዜ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ባለቤት ከሆነች ይኸው ሁለት ቀናት አልፈዋል።

ድሉ ያስከተለው የደስታ ስሜት በእግር ኳስ አፍቃሪው የጀርመን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በመላይቱ ሀገር አሁንም ገና እንደደመቀ ነው። የመገናኛ ብዙኃንም ብዙ እያሉበት ነው። በውጭውስ ዓለም ያለው አስተያየት ምን ይመስላል?

እንደሚታወቀው፣ ጀርመናውያን በሌሎች ሀገራት ከስራ ወዳድነታቸው እና ከከፍተኛ የማደራጀት ችሎታቸው ጎን በብዛት የሚታወቁት ዝግ እና የማይመቹ በመሆናቸውም ነው። እና የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በብራዚል የዋንጫ ግጥሚያ ላይ ያሳየው ማራኪ እና ጠንካራ የአጨዋወት ስልት እና ዲሲፕሊን ፣ በሌሎች ሀገራት ውስጥ ስለ ጀርመን ያለውን አመለካከት ምን ያህል ይቀይረዋል? የለንደን፣ ፈረንሳይ እና ዋሽንግተን ወኪሎቻችን በየሚኖሩባቸው ሀገራት ያለውን አስተያየት እንዲነግሩን ጠይቄአቸዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነህ፣ ሀይማኖት ጥሩነህ፣ አበበ ፈለቀ፣

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic