ከቤጂንግ የመጀመርያዉ ወርቅ በገንዘቤ | ስፖርት | DW | 25.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ከቤጂንግ የመጀመርያዉ ወርቅ በገንዘቤ

24 ዓመትዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በቤጂንግ የዓለም አትሌቲክ ሻንፒዮን ለኢትዮጵያ የመጀመርያዉን የወርቅ ሜዳልያ አስገኘች። ገንዘቤ ዛሬ በተሳተፈችበት የ1500 ሜትር ሩጫ ዉድድር 4 ደቂቃ 8: 09 በሆነ ዉጤት በአንደኝነት አጠናቃለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

ከቤጂንግ የመጀመርያዉ ወርቅ በገንዘቤ


በሁለተኛነት ኬንያዊት አትሌት የብር ሜዳልያ በጅዋ ስታስገባ፤ በሶስተኝነት ትዉልደ ኢትዮጵያዊት የኔዘርላንድ ዜጋ ሲፋን ሃስን የነሃስ ሜዳልያ አግኝታለች። አትሌት ገንዘቤ ገና የ 5000 ሺ ሜትሩን ዉድድር ተካፍላ ወርቁን ኪስዋ ለማስገባት ዝግጅት ላይ መሆንዋም ተዘግቦአል። ባለፈዉ ቅዳሜ የጀመረዉና የፊታችን እሁድ በሚጠናቀቀዉ በቤጂንጉ ዉድድር ኬንያ እስካሁን በ6 ሜዳልያ ዉድድሩን እንደምትመራl፤ ኢትዮጵያ ደግሞ በሁለት ብር 11 ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ትናንት በሳምንታዊ የስፖርት ዘገባችን ላይ መዘገባችን ይታወቃል። የኢትዮጵያን በቤጂንግ የአትሌቲክ ሻንፒዮና ዉድድር የሜዳልያ ብዛት ደረጃዋ ከፍ ይል ይሆን፤ የፓሪስዋ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነህ ገንዘቤ ዉድድሩን ካሸነፈች በኋላ የነገንዘቤን ቡድን የሚመሩትን አሰልጣኝ ንጉሴ ጌቻሞን ከቤጂንግ በስልክ አነጋጋግራ ዘገባ ልካልናለች።


ሐይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic