ከባድ የመሪት መንቀጥቀጥ በደቡባዊ እስያ | ዓለም | DW | 26.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ከባድ የመሪት መንቀጥቀጥ በደቡባዊ እስያ

በደቡባዊ እስያ ከፍተኛ የመሪት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። በተለይ አፍጋኒስታን ደቡባዊ ክፍል ፋሲባድ ከተማ የተከሰተዉ የመሪት ርዕደት በሪክተር መለክያ 7,5 መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ።

በሰሜን ምሥራቅ አፍጋኒስታን በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ 150 ሰዎች ሞታቸዉ ነዉ የተዘገበዉ። በሰሜን ፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የአፍጋኒስታን የታክሀር ግዛት የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከ ሕንድ ኒው ዴሊ ከተማ ድረስ መሰማቱን የሕንድ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ተያይዞ የወጣው ዜና አመልክቶዋል። በአካባቢው ተማሪዎች ከአደጋው ለማምለጥ ከትምህርት ቤታቸውን ሲውጡ በተፈጠረው ግፊያ እና ጭንቅንቅ ወቅት ቢያንስ 12 ልጃገረዶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ