ከባለሥልጣናት ግድያዎች ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ | ኢትዮጵያ | DW | 26.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከባለሥልጣናት ግድያዎች ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

 ስድስት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ከታሰሩት መካከል የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አመራር እና አባላት፣የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ይገኙበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58

ከታሰሩት መካከል የኢሳት ጋዜጠኛ ይገኝበታል

ሰኔ 15፣2011 ዓመተ ምህረት ባሕር ዳር እና አዲስ አበባ በተፈጸሙት የከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያዎች ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የተባሉ ሰዎች አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።  ስድስት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ከታሰሩት መካከል የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አመራር እና አባላት፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ጋዜጠኛ ይገኙበታል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic