ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ የገንዘብ ርዳታ በኦሮሚያ  | ኢትዮጵያ | DW | 09.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ የገንዘብ ርዳታ በኦሮሚያ 

ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ሰዎች መርጃ በመቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ መሰባሰቡን  የኦሮሚያ መስተዳድር ባለሥልጣናት አስታወቁ። ለርዳታዉ ተብሎ በተከፈቱ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ከ315.5 ሚሊዮን ብር በላይ መግባቱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሐላፊ አቶ አድሱ አረጋ ባለፈዉ ሰኞ በፌስቡክ ገጻቸዉ አስፍረዉ ነበር።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በተከሰተዉ ግጭት ሳቢያ ከ55ሽ በላይ ሰዎች ከቄያቸዉ ተፈናቅለዋል።ተፈናቃዮቹን ለመርዳት አገር ዉስጥም ሆነ ዉጭ  የሙዚቃ ድግሶችን ከማዘጋጀት እስከ ጨርቅ  አንጥፎ ገንዘብ መሰብሰብ ድረስ ጥረት ተደርጓል።

በክልሉ በሚንቀሳቀሱ አራት ባንኮች ይህን የገንዘብ ርዳታ የማስተባበርና የማቀናጀት ሚና እየተወጡ እንደምገኙ ለመረዳት ተችለዋል። በነዚህ ባንኮች የተከፈቱ የሒሳብ ቁጥሮች ላይ እስከ ሰኞ ድረስ ከ315.5 ሚሊዮን ብር በላይ መግባቱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሐላፊ አቶ አድሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸዉ አስፍረዉ ነበር።

የሰዎች መፈናቀል ይፋ እንደሆነ የኦሮሚያ የሕብረት ስራ ባንክ ሰራተኞች ወደ 3.7 ሚሊዮን ብር እንዳዋጡ የባንኩ የጥናትና ኩሙኒክሼን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ በበኩላቸዉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ የሕብረት ስራ ባንክ በተከፈተዉ የሒሳብ ቁጥር ላይ ትላንት እስከ 10 ሰዓት ድረስ ገቢ የሆነዉ 153.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን አቶ ጋማዳ ኦላና በበኩላቸዉ ለዶይቼ ቬሌ የላኩት መልክት አመልክተዋል።

የሚሰበሰብ ገንዘብ ለተፈለገዉ ዓላማ መዋሉ አለመዋሉ እምነታቸዉንና ጥርጣሬያቸዉን በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክ ገፅ ላይ አጋርተዋል። አብድዩ ጎዳናናግታቸዉ ኢላላ የምል የፌስቡክ ስም የያዙ ከምንጊዜውም በላይ ኃላፍነትና የሕዝብ ወጋነዊነት የሚሰማው አመራር አለ፣ የኦሮሚያ ህዝብ በመሪዎቹ ላይ እምነቱን ጥሏል፣  መሪዎቻችን በርግጠኝነት ለሕዝቡ የተሻለ ነገር እያሰቡ ነቸው ይላሉ። አቡደረስ ቀዉስሳት የምል የፌስቡክ ስም ያላቸዉ ደግሞ እንድህ አይነት ችግር ስፈጠር በብዙ አጋጣሚዎች እርዳታ ይሰበሰባል፣ ግን ወደ ተፈለገ ቦታ መድረሱን ይጠራጠራሉ።

ባንኩ የተሰበሰበዉ ገንዘብ ወደ ተፈለገዉ ቦታ መድረሱንና አለመድረሱን የሚቆጣጠርበት ስልት አለዉ ወይ በማለት አቶ በለጠንና አቶ ጋማዳን ጠይቀያቸዉ ነበር። ሁለቱም የባንኩ ሚና የገንዘብ ርዳታዉን መለገስ ለሚፈልጉ ሁኔታዎችን አመቻችቶ ገንዘቡን ገቢ እንድያደርጉ ማድርግ ነዉ እንጅ ሌላ «ስልጣን የለንም» ይላሉ። የርዳታ ስራዉን እንድያስፈፅም በክልል ደረጃ የተቋቋመዉ አስር አባል ያለዉ ኮሚቴ ላይ «እምነት» እንዳላቸዉም ጠቅሰዋል።

የኦሮምያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ሊቀመንበር  ሼክ አህመድ ዛክር ሼክ አህመድ ሳለህ የኮሚቴዉ አባል ናቸዉ። እሳቸዉ እንደሚሉት አሁን ኮሚቴዉ የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋም ስራ ላይ ተጠምዷል። ገንዘቡ ለፈተለገዉ አለማ ላይ ለማዋል ምን ያህል ግልፅነት አለ ለምለዉ ጥያቄ? ሼክ አህመድ ዛክር ሼክ አህመድ ሳለህ: «አሁን እዉነት ለመናገር፣ እየተሰጠ ያለዉ የገንዘብ ርዳታ የመንግስት የሒሳብ ቁጥር ላይ አይገባም። የሃይማኖት አባቶች በዝህ ኮሚቴ መሳተፋቸዉም ርዳታዉ በእምነትና በግልፅነት ለተረጅዎቹ እንድናስተላልፍ ነዉ። የፈጣሪ ፍራሃት ኖሮን ይህን ርዳታ በተዓማንነት ለማህበረሰቡ የማድርስ ስራ ዉስጥ ገብተን ነዉ ያለነዉ።»

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል መስተዳደሮችና የአገር ሽማግሌዎች ለግጭቱ መፍትሄ ለመስጠት ከአንዴም ሁለቴ ቢገናኙም እስካሁን ግጭቱንና የፀጥታ ስጋቱን መግታት እንዳልቻለ የፖለትካ ተንታኞች ያስረዳሉ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ