ከሳዑዲ ተመለሾች ሁኔታ | ኢትዮጵያ | DW | 22.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከሳዑዲ ተመለሾች ሁኔታ

የሳዑዲ ኣረብያ መንግሥት «ሕገወጥ ያላቸዉ» የዉጪ ዜጎች አገሩን ጥለዉ እንድወጡ የሰጣቸዉ ቀነ ገደብ ሊያልቅ ጥቅት ቀናቶች ይቀራሉ። እስካሁን  ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ይኖራሉ ተብለዉ ከሚገመቱት 400,000 ኢትዮጵያዉያን መካከል 83,000 ሺዉ  የጉዞ ሰነድ መዉሰዳቸዉ የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አድረጓል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

የሳዑዲ ተመለሾች

ከ83,000 ዉስጥም 30,000 ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸዉ ተጠቅሰዋል። የሳዑዲ መንግስት በ2006ም ሕገወጥ ያላቸዉን ከ160,000 በላይ ኢትዮጵያንን ወደ ሐገራቸዉ መመለሱ ይታወሳል። መርጋ ዮናስ ወደ አገር የተመሱትን በምን ሁታ ላይ እንደሚገኙ በመጠየቅ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ ሲመለሱ  እነሱን ለማቋቋም የሥራ እድል እንደሚፈጥርላቸዉ፣ እንድሁም የሚሰሩበትን መሬትና የገንዘብ ብድር እንደምያመቻችላቸዉ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  የህዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ባለፈዉ ሳምንት ይሕንኑ አረጋግጠዉ ነበር።

በ2006ም ሆነ አሁን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱያሉበትን ሁኔታ እንድያስረዱን አነጋግረን ነበር።

በከሚሴ  ነዋሪ መሆናቸዉን የተናገሩት ግን ስማቸዉ  እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ግለሰብ ከሳዑዲ አረቢያ  ከተመለሱ ገና ስምንት ቀናቸዉ መሆኑን ይናገራሉ። በሳዑድ አራብያ ሁለት ዓመት መቆየታቸዉን የሚናገሩት እኝሕ ግለሰብ በፍየል ማገድ ስራ ላይ ተሰማርተዉ እንደነበሩ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

መንግስት በአገርቱ ላሉት ወጣቶች 10 ቢሊዮን ብር በመመደብ በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተዉ እንዲሰሩ ኢያደረኩ ነዉ ሲል ተሰምተዋል።

በ2006 ወደ ኢትዮጵያ ከተላኩት ዉስጥ አንዱ ነኝ ያሉን የወልድያ ነዋሪ ከአጭር ጊዜ በዋላ ወደ ሳዑድ ደግም መመለሳቸዉን ይናገራሉ። በሳዑዲም በፍየል ማገድና ዳቦ መጋጋር ስራ ላይ ተሰማርተዉ እንደነበሩም ይናገራሉ። ይሁን እንጅ ከአምስት ወር በፊት በሳዑድ ፀጥታ አስከባሪዎች ተይዘዉ ወደ እትዮጵያ መላካቸዉን ጠቅሰዋል።

«የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገም። እንዳውም የቀበሌ መታወቂያ ድረስ ነው የተከለከነው» ሲሉም በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገፅ ላይ ልኮልናል። 

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic