ከሳውዲ የሚወጣ ገንዘብ እና የመንግሥት ውሳኔ  | ዓለም | DW | 24.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ከሳውዲ የሚወጣ ገንዘብ እና የመንግሥት ውሳኔ 

የሳውዲ የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ በትዊተር ባሰራጨው መልዕክት ሳውዲ አረብያ ወደ ሀገርዋ በሚገባ እና በሚወጣ ገንዘብ ነጻ ዝውውር እንደምትጸና አስታውቋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

ከሳውዲ የሚወጣ ገንዘብ እና የመንግሥት ውሳኔ 

የሳውዲ አረብያ መንግሥት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገንዘብ ሲልኩ ቀረጥ እንዲጣልባቸው የቀረበለትን ሀሳብ ተግባራዊ እንደማያደርግ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታወቀ ። ሹራ የተባለው የዘውዳዊው ስርዓት አማካሪ ምክር ቤት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሚልኩት ገንዘብ ላይ 6 በመቶ ቀረጥ እንዲከፍሉ ባለፈው ዓመት ሀሳብ አቅርቦ ነበር ። ይሁንና የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባለፈው እሁድ በትዊተር ባሰራጨው መልዕክት ሳውዲ አረብያ ወደ ሀገርዋ በሚገባ እና በሚወጣ ገንዘብ ነጻ ዝውውር እንደምትጸና አስታውቋል ። በጉዳዩ ላይ የሪያዱን ወኪላችንን ስለሺ ሽብሩን ቀደም ሲል በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። 
ስለሺ ሽብሩ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic