ከሳሽ ያጡት እነኤልያስ ለጠ/ሚኒሥትሩ አቤቱታ አቀረቡ | ኢትዮጵያ | DW | 08.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ከሳሽ ያጡት እነኤልያስ ለጠ/ሚኒሥትሩ አቤቱታ አቀረቡ

ከአምስት ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒሥትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአቤቱ ደብዳቤ ፃፉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:07

ኤልያስ ገብሩ እና ዳንኤል ሺበሺ ለጠ/ሚኒሥትሩ አቤት አሉ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከደነገገው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የታሰሩት ኤልያስ እና ዳንኤል እስካሁን በይፋ ክስ አልተመረተባቸውም። በእስር ላይ «ተጉላልተናል» ያሉት ጋዜጠኛ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒሥትሩ ለፃፉት የአቤቱታ ደብዳቤ የሚሰጣቸው ምላሽ የታወቀ ነገር የለም። አዲስ አበባ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ያነጋገራቸው የተጠርጣሪዎቹ ባልደረባ አቶ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገቢውን የሕክምና ክትትልም አለማግኘታቸው ተናግረዋል። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር 
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic