ከምረቃ በኋላ የሚጀምረው አዲስ የህይወት ምዕራፍ | ባህል | DW | 17.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ከምረቃ በኋላ የሚጀምረው አዲስ የህይወት ምዕራፍ

በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከተለያዩ የከፍተኛ ተቋማት ተመርቀዋል።ወጣቶቹ ገና በደስታ መንፈስ ውስጥ ቢገኙም ግን በቅርቡ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ይጠብቃቸዋል። የዩንቨርስቲ ህይወት ካበቃ በኋላ ህይወት እንዴት ይቀጥላል?

Hauptcampus der Universität Addis Abeba AAU

ቢያንስ ከ ሶስት ዓመት የዮንቨርስቲ ቆይታ በኋላ፤ በሂሳብ አያያዝ ሙያ፣ በህክምና፤ መምህንድስና፣ እና ሌሎቹም የሙያ ዘርፎች ተመርቀው ፤ ብዙዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሰሞኑን ከእጅ አስገብተዋል። ወጣት አብይሰሎም ላውጋው ከሁለት ሳምንት በፊት ከተመረቁ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው። አብይሰሎም ፈተናውን ካለፈ እዛው በተማረበት ዮንቨርስቲ ረዳት መምህር ሆኖ የመቀጠል እድል አለው፤ ካልሆነ ደግሞ ሌላ ስራ አፈላልጋለሁ ይላል። ብዙ ወጣቶች ተመርቀው እንደጨረሱ ወዲያው ስራ ካላገኙ፤ ተመልሰው ወላጆቻቸው ቤት ገብተው መኖሩ ግድ ይላቸዋል። ትልቁ ጥያቄያቸው ግን ከተመረቁም በኋላ ለምን ያህል ጊዜ ከወላጆቻቸው እጅ መጠበቅ እንዳለባቸው ነው። ሌላው በርካታ ተመራቂዎች የሚገጥማቸው ፈተና የመጀመሪያ የከፍተኛ ተቋም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፤ በንባኤ ቃል የሚያውቁት እና የስራው ዓለም በተግባር እጅጉን የተራራቀ ሲሆን፤ ወይም ጨርሶ በተማሩት የሙያ ዙርፍ ስራ ሳያገኙ ሲቀሩ ነው።ከዘንድሮ ተመራቂዎች አንዱ የሆነው ቁምላቸው እንዳለም እንደ አብይሰሎም በተማረበት ዮንቨርስቲ ረዳት መምህር ሆኖ ለማገልገል በአሁኑ ወቅት እየተወዳደረ ይገኛል።

የትምህርት ቤት ህይወት

የትምህርት ቤት ወይም የካምፓስ ህይወት ወጣቶች ከሚማሩት ትምህርት ባሻገር ብዙ ነገር የሚቀስሙበት አጋጣሚ ይፈጥራል። አንዳንዶች የሚቆጫቸው ሱስ እና የመሳሰሉትን ተምረው ሲወጡ፤ ሌሎች ደግሞ ከሌሎች ጥሩ ነገር ቀስመው ይወጣሉ፤ ቁምላቸውን በወልድያ ዮንቨርስቲ ቆይታው ከሰው ጋር ተሳስቦ መኖርን ተምሮ እንደወጣ ነግሮናል።

እያንዳንዱ ተማሪ ለ3 ዓመታት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር አብሮ በሚኖርበት ወቅት የትምህርት ቤት ጓደኞች ያፈራል። ይሁንና ይህ ከምረቃ በኋላ በህይወት ከሚቀየሩ ነገሮች አንዱ ነው ። አንደኛው ወይ ስራ አግኝቶ ፣ ሌላኛው ስለ ለመፈለግ ወደ ወላጆቹ ቤት ይመለሳል ሌላም ሌላም። ከዛም በዕረፍት ሰዓት እየተገናኙ የዮንቨርስቲ አይነቱን ህይወት መኖሩን ከባድ ያደርገዋል።

አርፋሴ አየለ፤ በሐዋሳ ዩንቨርስቲ በፊሳብ አያያዝ ሙያ ወይም አካውንቲንግ ተመርቃለች። «የምፈልገው የራሴን ስራ መስራት ነው» ትላለች፤ እንደ አርፈሴ የሀዋሳ ዮንቨርስቲ ምሩቅ የሆነው አብዱል ከሪም ግርማ የተመረቀው በህክምና ሙያ ነው። ከስድስት አመት የዮንቨርስቲ ቆይታ በኋላ የስራውን ዓለም ሊቀላቀል ተዘጋጅቷል።ስራ ማፈላለግ ግን አያስፈልገውም።

ጥቂት ተመራዊዎች የዩንቨርስቲ ህይወት ካበቃ በኋላ ህይወት እንዴት እንደሚቀጥል እና ስለ አዲሱ የህይወት ምዕራፋቸው አካፍለውናል። ዘገባውን በድምፅም ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች