1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦዲፒና ኦነግ ችግሮችን ለመፍታት ተስማሙ

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በመካከላቸው የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸዉ ተነገረ። ስምምነቱ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ ላይ መፈፀሙ ነዉ የተነገረዉ።  

https://p.dw.com/p/3BzJ6
Äthiopien Treffen Volksgruppe der Oromo Dawud Ibssa
ምስል DW/S. Muchie

የቴክኒክ ኮሚቴው ከምሁራን፣ ከአባ ገዳዎች፤ ከኦዲፒና ከኦነግ አባላት አሉት

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በመካከላቸው የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸዉ ተነገረ። ስምምነቱ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ ላይ መፈፀሙ ነዉ የተነገረዉ።  በእርቅ ዉይይቱ ላይ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል። በዛሬዉ የእርቀ ሰላም መድረክ   71 አባላት ያለው የቴክኒክ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፥ የቴክኒክ ኮሚቴውም ከምሁራን 11፣ ከአባ ገዳዎች 54፣ ከኦዲፒ 3 እንዲሁም ከኦነግ 3 አባላት ያለው መሆኑ ታዉቋል።  


ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ