ኦነግ በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ወሰደ የተባለዉ ርምጃ  | ኢትዮጵያ | DW | 19.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኦነግ በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ወሰደ የተባለዉ ርምጃ 

በኦሮሚያ ክልል በቦራና ዞን በሞያሌ ከተማ የመከላክያ ሰራዊት ካደረሰው ጥቃት በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወደ ጎረበት ኬንያ እየተሰደዱ እንደሚገኙ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:23

ኦነግ ወሰደ የተባለዉ ርምጃ 

ርምጃዉ የተወሰደው የኦሮሞ ነፃ አዉጭ ግንባር /ኦነግ/ ወታደሮች በአከባባዊ ይገኛሉ በሚል «በተሰሳተ መረጃ» ላይ በመመስረት መሆኑንን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስክርታርያት ተወካይ ሌተና  ጀነራል ሃሰን ኢብራሂም በመንግስት መገናኛ ብዙሀን ላይ ተናግረዋል።

Karte Äthiopien englisch

በሽህዎች የሚቆጠሩ የሞያሌ ነዋርዎች ወደ ኬንያ-ሞያሌ የመሰደዳቸዉ ሰበብ የመከላክያ ሰራዊት የፈጠረዉ የደህንነት ስጋት መሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል። በተቃራንዉ ደግሞ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀነራል ፣አሰፋ አብዮ «ኦነግ በአከባቢው እርምጃ ለመውሰድ ከፍተኛ ዘመቻ እና ውዥንብር በመፍጠሩ» ሰዎች ሰግተዉ ለስደት ተዳርገዋል ብለዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ ካለፈዉ ሳምንት አንስቶ ኦነግ በመከላክያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት አድርሷል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው። በተለይም በቀለም ወለጋ ዞን በግዳም አከባቢ፣ እንድሁም በምዕራብ ወለጋ ዞን በቤጊ አከባቢ የኦነግ ሰራዊት ወሰደ በተባለዉ እርምጃ በመከላክያ ሰራዊት አባላትና በተሽከርካሪዎቻቸዉ ላይ ጥቃት ማድረሱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ትናንት ከሰዓትና ሌሊት ሆነ ያሉትን እኚህ የአይን እማኝ ነግረውናል: «ጥቃቱ የተጀመረዉ ትላንት ወደ 9 ሰዓት ነዉ። ቦታዉም በቀለም ወለጋ ዞን በግዳም ወረዳ በቀለምንና በግራይ ከተማ መከካከል ማርቻ በመባል የምታወቅ ወንዝ ላይ ነዉ። የመከላክያ ሠራዊቱ በዛ እያለፉ ሳሉ፣ የኦነግ ሰራዊት ደግሞ በወንዙ ላይ ይዞት ነበሩ። በዚህ ቦታ ላይ በተካሄደዉ ጥቃት ሁለት ኦራል ተብሎ የሚጠረ ተሽከርካር ላይ የነበሩ ጥቃት ደርሶባቸዋል። አንድ ኦራል ማምለጥ ሲችል ሌላዉ ግን ከነ መከላክያ ሠራዊቱ አባላት ተቃጥለዋል።»

 

ሌላኛዉ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ ከሰዓት ይህ ጥቃት መፈፀሙን ተናግሮ ትላንት ምሽት ላይ ሌላ ጥቃት እንደደረሰም እንድህ አስረድተዋል፣ «ትላንት ምሽት ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ በኮቦርና ቃሽማንዶ ከተማ ማካከል አንድ የነዳጅ ቦቴን አጂቦ ወደ አሶሳ ሲሄዱ የነበሩ ኦራልና ፒክአፕ ተሽከርካር ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።»

በዚህ አከባቢ ተፈፀመ የተባለዉን ጥቃት ያረጋገጡት የቤጊ ከተማ የፀጥታ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ሃሩን በቀለ ናቸዉ። ስለ ጥቃቱ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት ሃላፊው ጉዳዩ በመጣራት ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ ተገልጸዋል: «በትላንትናዉ እለት  መከላክያ በዚህ አልፎ ወደ ግዳሚ ሄዶ ነበሩ። ቀለም የተባለዉ ቦታ ካለፉ በኋላ መከላክያ ላይ ቱክስ መከፈቱን መረጃ አግኝተን ነበር። ምሽት አከባቢ ደግሞ ለመከላክያ ዉሃ አድርሶ በመመለስ ላይ የነበረ አንድ ቦቴና ፒካፕ ላይ ቱክስ መከፈቱን መረጃ አግንተኝ ነበር። ስለ ጥቃቱም ሆነ የተጎዱ ካሉ ለማጣራት ሰዎችን ልከናል።»

ሁለቱም የአይን እማኞች ከጥቃቱ በኋላ ህዝቡ ፍርሀት ዉስጥ እንደሚገኝም ገልጸው፣ ሰዉ ኢየታሰረ፣ ኢየተገረፈ እንደሆነም ተናግረዋል። 

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች