ኦብነግ ሰላምና ልማትን መረጋገጥ እንደሚሰራ ገለፀ | ኢትዮጵያ | DW | 04.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኦብነግ ሰላምና ልማትን መረጋገጥ እንደሚሰራ ገለፀ

ለኦጋዴን ነፃነት ሲታገል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ኦብነግ በሶማሌ ክልል ሰላምና ልማትን ለመረጋገጥ እንደሚሰራ ገለፀ።ይህ የተገለጸዉ በሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ሶዴፓ ሰሞኑን ባካሄደዉ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በተጋባዥነት የተገኙት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር/ኦብነግ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ በጉባኤዉ ማጠቃለያ ባሰሙት ንግግር ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

የተጀመረው ለውጥ የፖለቲካዊ ዓላማችንን በሰላማዊ መንገድ እንድናራምድ አድርጎናል

ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በኤርትራ መሽጎ ለኦጋዴን ነፃነት ሲታገል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር/ኦብነግ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከመንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት ሀገር ቤት ከገባ ወራት አስቆጥሯል። የሶማሌ ክልልን በመምራት ላይ የሚገኘው እና በአዲሱ ስያሜው የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ሶዴፓ ባካሄደው የሰሞኑ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በተጋባዥነት ተገኝቶ ነበር። የግንባሩ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙር በፓርቲው የማጠቃለያ መድረክ ላይ ግምባሩ ለክልሉ ሰላምና ልማት መረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል ። በጠቅላይ ሚንስትሩ የተጀመረው ለውጥ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡም ሆነ ፖለቲካዊ ዓላማችንን በሰላማዊ መንገድ እንድናራምድ አድርጎናል ያሉት ሀላፊው ከመንግስት ጋር የገቡትን ስምምነት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። ግንባሩ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ከአንድ ሺ ስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ ወታደሮቹን የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ወደ ማሰልጠኛ ማስገባቱንና ከስልጠናው በኃላ በሶማሌ ክልል የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ገብተው እንደሚሰሩ መግለፁ የሚታወስ ነው።


መሳይ ተክሉ 


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች