ኦባማ የጋበዟቸው 13 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች | ባህል | DW | 05.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኦባማ የጋበዟቸው 13 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

« young african leaders initiative » በሚለው የዩኤስ አሜሪካ መርሃ ግብር ስር 500 ወጣት አፍሪቃውያን ተመርጠዋል። ከነዚህም ውስጥ 13ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከነዚህ በቅርቡ ወደ ዩናይትድ ስትቴስ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ካሉ ወጣቶች መካከል ሶስቱን በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅቷ አነጋግረናቸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:17
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:17 ደቂቃ

ኦባማ የጋበዟቸው ወጣት ኢትዮጵያውያን

እኢአ ከ 2010 ዓ ም ጀምሮ የዮናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ ጠቃሚ ድርሻ ሊያበረክቱ የሚችሉ ወጣት አፍሪቃውያንን ለማበረታታት መርሃ ግብር ጀምረዋል። በዚህም መሠረት ዘንድሮም ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት የተውጣጡ 500 ወጣት አፍሪቃውያንን በሰኔ ወር ወደ አሜሪካ ጋብዘዋል።

ከኢትዮጵያ በጠቅላላው 1700 ወጣቶች በዚህ መርሃ ግብር ለመሳተፍ መወዳደራቸውን የአዲስ አበባው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ድረ ገፁ ላይ ሰፍሯል። በመርሃ ግብሩ ለመሳትፍ መስፈርቶቹ ምን እንደነበሩ ሄርሜላ ታብራራለች፤

በዩናይትድ ስቴትስ መርሃ ግብር መሠረት ለአፍሪቃ እድገት እና ብልፅግና ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ተብለው ዘንድሮ ከተመረጡት 13 ኢትዮጵያውያን መካከል፤ የ 27 ዓመቷ ሄርሜላ ወንድሙ አንዷ ናት። እንደ ሄርሜላ በመመረጡ ደስ የተሰኘው ሌላው ኢትዮጵያዊ የ 32 ዓመቱ ዳኛቸው ቦጋለ ነው። ዘንድሮ ከተመረጡት 9 ሴት ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ ሌላኛዋ ወጣት ደግሞ ህሊና ብርሀኑ ትባላለች።

ከ 500 አፍሪቃውያን ወጣቶች አንድ መቶው እንደ ዳኛቸው በሁለት ተቋማት የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ። ከኢትዮጵያ ዳኛቸውን ጨምሮ አራት ወጣቶች የዚህ እድል ተካፋይ ይሆናሉ። ወጣቶቹ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ዮናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ በዝጅግት ላይ ናቸው። እዛም በሚሄዱበት ጊዜ ስለሚኖራቸው ቆይታ እና ከመርሃ ግብሩ የሚጠብቁትን ገልፀውልናል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic