ኦባማ ለአፍሪቃውያን | ኢትዮጵያ | DW | 21.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኦባማ ለአፍሪቃውያን

በአገሪቱ ከሁለት መቶ ዓመታት የበለጠ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አፍሪቃዊ የዘር ግንድ ያለው መሪ የስልጣኑን ቁንጮ ተቆናጧል፥ በአሜሪካ። ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዓለም ብዙ ይጠብቃል። በተለይ ደግሞ አፍሪቃ ከገባችበት የሙስና፣ የአስተዳደር ብልሹነትና የሠብዓዊ መብት ጥሰት አደገኛ ህመም ሊፈውሷትም ይችሉ ይሆናል ተብለው ተጠብቀዋል።

ከኦባማ በስተኋላ፥ ቡሽና ባለቤታቸው

ከኦባማ በስተኋላ፥ ቡሽና ባለቤታቸው

ትናንት ምሽት የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ከፈፀሙት ባራክ ኦባማ፤ አፍሪቃ በአያሌው እንደምትጠብቅ ታዋቂ የሆኑ ፖለቲከኞችና ግለሰቦች እየገለፁ ነው። የቀድሞው የአፍሪቃ አንድንነት ዋና ፀሀፊ ሳሌም አህመድ ሳሌምና ኬንያዊቷ የሠላም ኖቤል ተሽላሚ ዋንጋሪ ማታይ ከምንም በላይ በአፍሪቃ ያሉ መሪዎች የአስተዳደር ብልሹነትን ማስወገድ አለባቸው ብለዋል። ሙስናን ሲታገሉና ሠብዓዊ መብትን ሲያከብሩ ያኔ አዲሱ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት አፍሪቃን ይረዳሉ ሲሉም ገልፀዋል።

ተዛማጅ ዘገባዎች