1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦሮሚያ፣ ብዙ አካባቢ ሕክምና ተቋረጠ፣ ትምሕርትም

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2011

የቢሮዉ ኃላፊ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለDW እንደነገሩት በምእራብ ጉጂ እና በአራቱም የወለጋ ዞኖች የሚገኙ የጤና ጣቢያዎች መደበኛ አገልግሎት እና የጤና ኤክስቴንሽን አቋርጠዋል። ሐኪሞች ግጭት እና ሑከቱን በመፍራት አካባቢዎቹን ጥለዉ ሸሽተዋል

https://p.dw.com/p/3ArJW
Äthiopien | Challenges of west Oromia health and education services
ምስል DW/S. Muchie

(Beri.AA) Oromia Region-Health services and schools disrupted - MP3-Stereo


የኦሮሚያ መስተዳድርን በሚያብጠዉ ግጭት እና ሁከት ምክንያት  በአብዛኛዉ አካባቢ መደበኛ የሕክምና አገልግሎት መቋረጡን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ዐስታወቀ። የቢሮዉ ኃላፊ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለDW እንደነገሩት በምእራብ ጉጂ እና በአራቱም የወለጋ ዞኖች የሚገኙ የጤና ጣቢያዎች መደበኛ አገልግሎት እና የጤና ኤክስቴንሽን አቋርጠዋል። ሐኪሞች ግጭት እና ሑከቱን በመፍራት አካባቢዎቹን ጥለዉ ሸሽተዋል። የአምቡላንስ አገልግሎት በመቋረጡም ወላጆች እስከሞት ለሚደረስ አደጋ ተጋልጠዋል። ኃላፊዉ አክለዉ እንዳሉት ደቡብ ኢትዮጵያ የሞያሌ ሆስፒታል ሲዘጋ፤ ምዕራብ ኢትዮጵያ ደግሞ የደንቢ ዶሎ ሆስፒታል ኦና ቀርቷል። ሆሮ ጉዱሩ እና ሐረርጌ የሚገኙ የጤና ተቋማትም የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም-ኃላፊዉ እንዳሉት። የኦሮሚያ ትምሕርት ቢሮ በበኩሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ዐስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ