እድሜ ይፍታህ ለቀድሞዉ የቻድ አምባገነን መሪ | ኢትዮጵያ | DW | 30.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

እድሜ ይፍታህ ለቀድሞዉ የቻድ አምባገነን መሪ

የቀድሞዉ የቻድ አምባገነን ፕሬዚዳንት ኢስኔ አብሬ እድሜ ይፍታህ ተፈረደባቸዉ። ዳካር ሴኔጋል ላይ የሚገኘዉ ልዩ የአፍሪቃውያን ፍርድ ቤት ቤት ዛሬ ባስቻለዉ ልዩ ችሎት የ 73 ዓመቱ ሃብሬ በስብዕና አንፃር የጭካኔ ርምጃን፣ በቁም ስቅል ማሳየት ተግባር፣ በግድያ እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ኢስኔ አብሬ ቻድን በገዙበት ከጎርጎረሳዉያኑ 1982 ዓ,ም እስከ 1990 ዓ,ም 40 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል፣ 10 ሺህ ሰዎች ደግሞ የግፍ በደል ተፈጽሞባቸዋል። የልዩው የአፍሪቃውያን ፍርድ ቤት ሊቀመንበር ዳኛ ጉስታቭ ካም እንዲህ በማለት አሳውቀዋል። ዳኛ ጉስታቭ ካም

« ፍርድ ቤቱ የወንጀሉን ክብደትና የኢስኔ አብሬን የግል ሁኔታ ሁኔታ ትኩረት ዉስጥ በማስገባት እና የወንጀሉን ክብደት በማመዛዘን እዚህ ዉሳኔ ላይ ደርሶአል። ፍርድ ቤቱ ኢስኔ አብሬ ላይ የእድሜ ልክ እስራት በይኖአል። ፍርድ ቤቱ የሃስኔ ሃብሬን ንብረት አይወርስም። ኢስኔ አብሬ፣ በፍርድ ቤቱ ብይን ወንጀል መቅጫ አንቀጽ 360 ን መሰረት፣ ፍርዱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ዉስጥ ይግባኝ ማስገባት እንደሚችሉ፣ ፍርድ ቤቱ አሳውቅዎታል። ይህ ነዉ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ። »

ብይኑ ይፋ ከሆነ በኋላ እጆቻቸውን ከፍ በማድረግ ለደጋፊዎቻቸው ሰላምታ የሰጡት ኢስኔ አብሬ ውድቀት ለፈረንሳይ አፍሪቃ » በማለት በአፍሪቃ ላይ ተፅዕኖ ታሳርፋለች ያሏትን የቀድሞ የቻድ እና የሴኔጋል ቅኝ ገዢ ፈረንሳይን ኮንነዋል። ከሳሾች ብይኑን በደስታ ሲቀበሉት፣ የኢስኔ አብሬ ደጋፊዎች አጣጥለውታል። የመብት ተሟጋቹ « ሂውመን ራይትስ ዎች» ደግሞ በፈፀሙት አስከፊው ወንጀል የተበየነባቸውን ዕድሜ ልክ እስራትን ለሰለባዎቻቸው ትልቅ ድል ነው ብሎታል።

አብሬ በ ጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ,ም ዛሬ ስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ካስወገዷቸው በኋላ ወደ ሴኔጋል መሸሻቸዉ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ