እደገትና የምርመራ ጋዜጠኝነት | ዓለም | DW | 20.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እደገትና የምርመራ ጋዜጠኝነት

በእድገት ወደፊት በመገስገስ ላይ ባሉትና ገና በማደግ ላይ ባሉት ሃገራት የኤኮኖሚ እድገት አማላይ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ህብረተሰቡንና ተፈጥሮን ለችግር ያጋለጠ ነው ። መንግሥትና ኤኮኖሚ ላይ የሚሰነዘሩት ችቶች ግ አይወደዱም ። ሆኖም አንዳንድ ጋዜጠኞች የዝህብ ቅሬታዎች ሰሚ እንዲያገኙ ያለሰለሰ ጥረት ከማድረግ አይቦዝኑም ።

ቦን ለ3 ቀናት ተካሂዶ ትናንት የተጠናቀቀው የዓለም ዓቀፉ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ የመነጋገሪያ ርዕስ « የወደፊት የእድገት እጣ ፈንታ » ነበር ። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮችና ፖለቲከኞች የተገኙበት ይኽው መድረክ በተለይም በእድገት ወደፊት በመገስገስ ላይ ባሉትና ገና በማደግ ላይ ባሉት ሃገራት መገናኛ ብዙሃን በኤኮኖሚ እድገት ውስጥ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ላይ ነበር ትኩረቱ። በነዚህ ሃገራት የኤኮኖሚ እድገት አማላይ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ህብረተሰቡንና ተፈጥሮን ለችግር ያጋለጠ ነው ። ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግሥትና ኤኮኖሚ ላይ የሚሰነዘሩት ችቶች ግን አይወደዱም ። ሆኖም አንዳንድ ጋዜጠኞች የዝህብ ቅሬታዎች ሰሚ እንዲያገኙ ያለሰለሰ ጥረት ከማድረግ አይቦዝኑም ። ከነዚህ 2 ቱ ለቦኑ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ልምዳቸውን አካፍለው ነበር ። እጎአ መስከረም 2008 በእስያ ግዙፍ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅሰውን ቻይናን ቅሌት አናወጣት ።

GMF Global Media Forum 2013

ሺንግ ጁ

ቁጥራቸው 300 ሺህ የሚደርስ ህፃናት በተመረዘ የዱቄት ወተት ምክንያት ታመሙ ። ሰበቡ የዱቄት ወተቱ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ፕሮቲን እንዳለው ለማስመሰል አምራቾቹ ሜላኒን የተባለውን መርዘኛ ንጥረ ነገር መቀላቀላቸው ነው ። ለደራሲው ሺንግ ጁ አንድ ቀን ፣ ይህን መሰል አደጋ ቻይና ውስጥ እንደሚደርስ ግልፅ ነበር ። ሺንግ በሃገሪቱ የምግብ ዋስትና ስለመታጣቱ ከዓመታት በፊት ባወጣው መፀሐፍ ላይ ስጋታቸውን ገልጾ ነበር ።« ስራ አስፈፃሚዎቹ የምርመራዮን ይዘት ያውቁ ነበር ።ሁኔታው ምን ያህል ከባድ እንደነበርና የዱቄት ወተት ቅሌት እንደሚደርስም ያውቁ ነበር ።»የመንግስት ብቸኛ እርምጃም መፀሐፉ ሊያሳስራቸው እንደሚችል ሺንግ ጁን ማስፈራራት ነበር ። ሺንግ አሁን በስደት ሙኒክ ጀርመን ነው የሚኖረው ። ናይጀሪያዊቷ ጋዜጠኛ ቶዮሲ ኦጉንሴዬ በናይጀሪያዋ የሌጎስ ከተማ ባካሄደችው የጋዜጠኝነት ምርመራ የተሳካ ውጤት አግኝታለች ። ሌጎስ የሚገኝ አንድ የብረት ብረት አምራች ፋብሪካ ፣ አካባቢን ክፉኛ እንደሚበክልና በነዋሪዎችም ላይ ካንሰር እንደሚያስከትል ደርሳበታለች ። በምርመራ ዘገባዋ ጉዳዩን ፍርጥርጥ አድርጋ በማውጣቷ ፋብሪካው ተዘግቷል ፤ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎችም የገንዘብ ካሳ ተሰጥቷቸዋል ።

GMF Global Media Forum 2013

ቶዮሲ ኦጉንሴዬ

እዚህ ላይ የተደረሰው ግን በቀላሉ አልነበረም ። ምርመራው በሚካሄድበት ጊዜ የኩባንያው ድርሻም ሆነ ኩባንያው ለናይጀሪያ እድገት ያበረከተው ድርሻ በፖለቲከኞች ተወድሷል ። ጋዜጠኛ ኦጉንሴዬ ግን ይህ ፍሬ ያለው ነገር ነው ተብሎ ሊሰፍር አይገባም ትላለች ።« የኤኮኖሚ ጥቅም ለህዝቡ መሆን ያለበት ነው የሚመስለኝ ። ሆኖም ከኤኮኖሚው ተጠቃሚ መሆን ያለበት ህዝብ የሚሞት ከሆነ ማነው ታዲያ የሚጠቀመው ? ከኤኮኖሚው የሚገኘው ጥቅምም ምንም ትርጉም አይሰጥም ። ምክንያቱም ህዝቡ ከታመመ ከኤኮኖሚው እድገት ምንም አያገኝምና »ለኦጉንሴዬ ትልቁ ስኬት ፋብሪካው መዘጋቱ ብቻ አልነበረም ። ህብረተሰቡም ፋብሪካው ለሕመም እንደዳረገው እንዲያውቅ ማድረጓም ጭምር እንጂ ። የምትሰራበት ጋዜጣም የጤና ችግሩን ለማጣራት የህክምና ምርመራውን ወጪ ሸፍኗል ። በናይጀሪያ ይህን መሰሉን ድጋፍ ማድረግ ግን የተለመደ አይደለም ።

ችግሩ የተጋለጠበት ጋዜጣ ቅጅዎች በሙሉ ተሸጡ በናይጀሪያ የተፈፀመው በይፋ ማጋለጥ ለቻይናዊው ሺንግ ጁ ህልም ነው ። በቻይና የመባልዕት ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለተፈፀመው ብልሹ አሰራር ያሳተሙት መፀሃፍ እጅግ ከፍተኛ ሳንሱር ተደርጎበታል ። በመፃህፍት መሸጫ ቤቶች በድብቅ ነበር የሚቀመጠው ። በህንፃ መሳሪያዎች ክፍል ነበር የሚቀመጠው ።« እንደ እድል ሆኖ መፀሐፉን ከሆንግ ኮንግ መግዛት ይቻል ነበር ። ፅሁፉን ወደ ሲዲ ገልብጦ መስጠትም ሌላው ውጤታማ የማሰራጫ መንገድ ነበር ። »እንደ አራተኛው የመንግሥት ኃይል ለዲሞክራሲ ትልቅ ሚና የሚጫወቱት ጋዜጠኞች በቻይና ስለ ኤኮኖሚ ብልሹ አሰራር ማውሳት ከፈለጉ ችግር አለባቸው ። መንግሥት የኤኮኖሚ ጥቅሞቹን ማስጠበቅ ይሻል ። ደራሲው ይህን መረጃ ማቅረብ የቻለው ከማስታወቂያ ና ከኤኮኖሚ ባሥልጣናት ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic