እየተንገዳገደ ያለዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር | አፍሪቃ | DW | 10.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

እየተንገዳገደ ያለዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እና በአገሪቱ «በሕጋዊ መንገድ ይንቀሳቀሳሉ» የተባሉት ተቃዋሚ የፖለትካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ድርድር ሥለሚሳተፉ ተጨማሪ ፓርቲዎች ትናንት መወያየታቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42

የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ድርድሩን መድረክና ኢህአዴግ ብቻ እንደሚያካሄዱት መግለጡ ተዘግቧል። በኢሕአዲግ በኩል ደግሞ ምክር ቤት ዉስጥ መቀመጫ ያላቸዉ እና የኢሕአዴግ አጋር የሚባሉ ፓርቲዎች በድርድሩ ይሳተፉ የሚል ሐሳብ አቅርቧል ተብሏል።የተቀሩት ተቃዋሚ  ፓርትዎች ግን ደስተኛ አለመሆናቸዉ ዘገባዉ አመልክተዋል። 

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)ን እና በአገሪቱ ዉስጥ ያሉት 20 ተቃዋሚ ፓርትዎች መካከል የሚደረገዉ ድርድር በትላንትና እለትም ቀጥሎ ተሳታፊ ፓርትዎች «እናማን ይሁኑ» የሚል ዉይይት መካሄዱ የኢትዮጵያ ደሞክራትክ ፓርት/ኢደፓ/ የስራ አስፈጻም አባልና የጥናትና ምርምር ሐላፍ  አቶ ዋስሁን ተስፋዬ ለዶቼ ቬሌ ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከኢህአዴግ ብቻ ጋር ለመደራደር መፈለጉን እንደ አቋም ይዟል። 21ዱን ፓርትዎች በአንድ መድረክ ላይ ሆኖ ይደራደሩ ከተባለ መድረኩ ከድርድር ይልቅ «ጉባኤ ወይም ሸንጎ» ይሆናል በማለት የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንደምክንያትነት አስቀምጠዋል። ደርድር ከሆነ በሁለት አካልና ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸዉ ወገኖች መካከል መደረግ አለበትም የሚሉት ፕሮፌሶር በየነ ፓርቲያቸዉ ጥያቄዉን ያቀረበበት ምክንያት ይናገራሉ።

መድረክ  ከኢህአዴግ የሚያደረገዉ የአንድ ለአንድ ድርድር ዉጤት ማምጣት ከተፈለገ ሌሎች ፓርትዎች አዳራዉ ለመድረክ መስጠት አለባቸዉ የሚለዉን የመድረክን አቁም እንዴት ትመለከቱታላቸዉ ብለን ሌሎቹን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ጠይቀን ነበር።

ድርድሩ ታዓማኒነት እንደኖረዉ «ነፃና ገለልተኛ አደራዳር» እንዲኖር እንጅ «መስፈርት ባልወጣለት ሁኔታ  እኬሌ ይወክለኝ ወይም መሪ ሆኖ ይደራደር/ አይደራደር የሚል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት «መኢአድ» አቋም እንደለለዉ የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለዶቼ ቬሌ ይናገራሉ።

ኢህአዴግ በድርድሩ ላይ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ሲጋብዝ  «አገር አቀፍ ፓርትዎችና የክልል ፓርትዎች ሆኖ በፓርላማ መቀመጫ ያላቸው» ብሎ ቅደመ ሁኔታ ማስቀመጡ በትላንትና እለት የመከራከርያ ነጥብ እንደነበረም አቶ ዋሲሁን ይናገራሉ።

አጋሪቱን ያለችበት የፖለትካ ቀዉስ መፍቴ ሊሆን የምችለዉ ከድርድር ይልቅ ሽምግልና መሆን አለበት የሚሉት የህግ ባለሙያዉ አቶ ተማም አባቡልጉ የተቀመጠዉ ቅደመ ሁኔታም ትክክል አለመሆኑን ይናገራሉ። በኢሕአዲግ በኩል  መረጃ  ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ 


 

Audios and videos on the topic