እየተበራከተ የመጣዉ አስከፊ የጭነት መኪና አደጋ | ኢትዮጵያ | DW | 09.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

እየተበራከተ የመጣዉ አስከፊ የጭነት መኪና አደጋ

ሲኖትራክ የተባለ ገልባጭ የጭነት ተሽከርካሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰቅጣጭ አደጋን እያደረሰ ለነዋሪዉ ስጋት መሆኑ ተገለፀ።

አንድ ኢትዮጵያዊ የኤሌክትሮ መካኒካል ባለሞያ እንደሚሉት ችግሩ ከተሽከርካሪዉ ጉድለት ሳይሆን ችግሩ እየተከሰተ ያለዉ በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ጉድለት ሳይሆን አልቀረም። የፊደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን በበኩሉ የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ችግር የሚለዉ መላምት ትክክል አይደለም። ይሁን እንጂ አሽከርካሪዎቹ የትራፊክ ሕግን አክብሮ ባለማሽከርከርና መኪናዉን ከአቅም በላይ ጭነት በማሸከም ነዉ፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል። እየተበራከተ የመጣዉን የመኪና አደጋ ችግር መንስኤዉን ለማወቅ አንድ የአጥኚ ቡድን ተቋቁሞ የችግሩን መንስኤ በማፈላለግ ላይ መሆኑም ተገልፆአል።


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic