እኛም እኮ አሜሪካዊያን ነን! | 1/1994 | DW | 09.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

1/1994

እኛም እኮ አሜሪካዊያን ነን!

ከ ኤፍ ቢ አይ ፣ ከፋይናንስ ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ይሁን ከሌሎች መስራቤቶች ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለን ሲል፤ አዳምስ የተባለው ድረገፅ ላይ ሰፍሯል። ADAMS « ALL DULLES AREA MUSLIM SOCIETY ይሰኛል።

default

መስከረም 1 ቀን ኒው ዮርክ

አዳምስ በዳላስ ፤ 5000 የሙስሊም ቤተሰቦችን ያቀፈ ማህበር ነው።« ለማረጋገጥ የምንፈልገው እኛም አክራሪ ሙስሊሞችን እንደምናወግዝ ነው» ይላሉ። የማህበሩ ቃል አቀባይ ሪዝዋን ጃካ። በድረ ገፁ ላይ በተጨማሪም የሴቶችን እኩልነት፣ እንዲሁም ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር በጋራ መስራቱን ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጡ አስምረውባቸዋል።

Muslime in den USA

አዳምስ የተሰኘው ማህበር

ይህም በቂ ምክንያት አለው። ከዋሽንግተን በስተ ደቡብ የሚኖረው የሙስሊም ህብረተሰብ እኢአ ከመስከረም 1 2001 ጀምሮ በቂ ጥላቻ ደርሶበታል። አማፂዎቹ ጥቃት ባደረሱ ምሽት አንድ የጥንት መስኪድ ውስጥ ሰብሮ በመግባት ለግንባታ የተቀመጡት እቃዎች ተቃጥለዋል። ይሁንና ጃካ እንደሚሉት- የሌላ እምነት ተከታዮች ይህ ሲሆን እቃዎች እንዳይጠፉ ተቆጣጥረዋል፤ የማህበሩ ሴቶች የሚያሰጋ ነገር ከገጠማቸው ለርዳታ ለመቆም ፍቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። በሙስሊሙ ላይ የሚደርስ ጥቃት እንደ ጃካ ሁሉ ሮበርት ማሮ በ አዳምስ ማህበር ሊቀመንበር ናቸው። ግራውንድ ዜሮ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ አቅራቢያ ሙስሊሞች የመገበያያ ቦታ ይሰራሉ ተብሎ በአደባባይ የተወራው ፖለቲካ ነው። « እንደዚህ አድርገው በቀላሉ ድምፅ ለማግኘት ነው።» በፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት አንድ ቄስ ቁራን አቃጠሉ የሚለውንም እንደዚሁ ተሰሚነት ለማግኘት ነው። ይላሉ ማሮ።

Muslime in den USA

ሪዝዋን ጃካ

የመገናኛ ብዙሀን ለዚህ ወሬ መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይሁንና ማሮ ተስፋ አልቆረጡም። መቼም ይሁን መቼ የአሜሪካ ሙስሊሞች ከማህበረሰቡ ጋር መዋሀዳቸው አይቀሬ ነው። ልክ እንደ ባለፉት መቶ አመታት እንደነበሩት ካቶሊኮች ጣሊያኖችም ሆኑ አየርላንዳውያን! ማሮ፤ ጆን ኤፍ ኬኔዲ የመጀመሪያው የካቶሊክ ፕሬዚደንት ሲሆነ የነበረውን ክርክር ያስታውሳሉ። በዛን ጊዜ የኬኔዲ ታማኝነት ለካቶሊኩ ቫቫስ ወይስ ላገራቸው አሜሪካ አከራካሪ ነበር። ሐይማኖት በ ዮስ አሜሪካ ምንም አይነት ሚና መጫወቱ እስኪቆም ገና አመታት ይቆጠራሉ። ሳሚራ ሁሴን ከመኪናዋ ፊት ፎቶ መነሳት አትፈልግም። ትውልደ ፍልስጤማዊዋ በሜሪላንድ ነው የምትኖረው። ጥሩ ተሞክሮ የላትም። ከጎልፍ ጦርነት ነው የምትጀምረው።« መጀመሪያ መኪናዎቻችንን አወደሙ፤ የቤት በሮቻችንን ሰባበሩ። ቁሻሻና የሞቱ ወፎች ወረወሩብን፤ አትክልቶቻችንን ሰባበሩብን።» ልጆቼ ትምህርት ቤት ይደበደቡ ወደቤት ሲመለሱም ይከታተሊዋቸው ነበር ይላሉ። ከ መስከረም 1 2001 ጥቃት በኋላ ደግሞ ችግሮቹ ይበልጥ ሆበ« ምንትጎመሪ ካውንቲ» ጸኑ። በማህበራዊ መስክ ያሉ ሰራተኞችም ይጨቆኑ ጀመር። መረጃና ጠቃሚ የሆኑ ስራዎችን ማካሄድ ሳሚራ ሁሴን የማህበራዊ ተሳትፎዋን ከመቼውም በበለጠ አጠናክራለች። በየትምህርት ቤቱ እየሄደች፤ ለተማሪዎችና አስተማሪዎች ለምን ሂጃብ እንደምታደርግ ትገልፃለች። መሳሪያዋ ትምህርት ነው።« እኔ ሰዎችን ማስረዳት ነው የምፈልገው። ከልጆች መጀመሩ ደግሞ ጥሩ ነው።» ልጆች ስለ ባህላቸውና ስለሐይማኖታቸው ከተረዱ ወላጆቻቸውም አመለካከታቸውን ይቀይራሉ። የሳሚራ ስራ የሚያስፈራ እንደነበር ዛሬ ሳሚራ ትገልፃለች።

Muslime in den USA

ሳሚራ ሁሴን

እኢአ በ2002 ዓ ም ከአከባቢዋ በፀረ-ገለልተኝነት ተሸልማለች። ቱፋኢል አህመድም አሜሪካዊ ሙስሊሞች ይበልጥ ከህብረተሰቡ ጋር እንዲተሳሰሩ የበኩሉን ያደርጋል። «ህንዶችና ፓኪስታኖች በትላልቅ ቤቶች ይኖራሉ ግን ድሆችን አይረዱም» ይላል አህመድ። የተወለደው ህንድ ነው። ኋላም ፓኪስታን ይኖራል። እኢአ 1973 ወደ ዮ ኤስ አሜሪካ ይሄዳል። የዛኑ መስከረም 1 2001 ዕለት እራሱን ለማሳተፍ ይወስናል። ከዛም የውይይት መድረኮች ይከፍታል። በመጨረሻም የጋራ ዕርዳታ መስጫወችን ያመቻቻል። ከሌሎቹ ከተሞች የተሻለ ከ 2001 ዓ ም ጀምሮ ሙስሊሞች በምንትጎመሪ ካውንቲ ምግብ ይሰበስባሉ። አህመድ እራሱ ያለምንም ዕፍረት የገበያው በራፍ ላይ ሆኖ እርዳታ ይለምናል። በየአመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምግቦች ይሰበሰባሉ። ከብቶች ሳይቀር አርደው ለተረጂዎች ሰጥተዋል። አህመድ ስጋት አለው። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት እዚህ አካባቢ ይበልጡን ናቸው። ግን የማህበራዊ እርዳታ የሚሰጡት ነጮቹ እንደሆኑ ተመልክተዋል? ብሎ ይጠይቃል አህመድ። ይህም ለውጥ እንዲያመሳ ጠንክሮ ይሰራል። በምንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ሙስሊሞች ሲነፃፀር የባሰ ጭቆና አይደርስባቸውም። ሶሪያይው 20 አመት ጀርመን ከኖረ በኋላ አሁን 10 ዓመት ሊሆነው ነው ዮ ኤስ አሜሪካ ሲኖር። የምንትጎመሪ ካውንቲ የሙስሊሞች ማህበር ዓባል ነው። 300-400 የሚሆኑ አባሎቻቸው አላማቸውን ያንቀሳቅሳሉ። «በዛ አካባቢ ሰዎች በቂ መረጃ አላቸው» ይላል ሀፊዝ። ወደ ቴክሳስ ወይም ደቡብ ቨርጅኒያ ሲኬድ እዛ አካባቢ የሚኖሩት ሰዎች ሶርያና ዮርዳኒያን የት እንደሆኑ እንኳን አያውቁም። ለመስከረም አንዱ ጥቃት ተጠያቂው ማን እንደሆነም አያውቁም።» ጉሌድ ካሲም እኢአ 1985፤ የ 10 ዓመት ልጅ ሳለ ነው ከሶማሊያ ወደ ምንትጎመሪ ካውንቲ የመጣው። ከቅርብ ጊዜ አንስቶ የሙስሊሙ ማህበር ፕሬዚዳንት ነው። ለአሜሪካ ውትድርና ሲያገለግል የነበረው ካሲም፤ እራስህን እንደ ሙስሊም ነው ወይስ እንደ አሜሪካዊ የምታየው ለሚለው ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፤ « በመጀመሪያ አንድን ክርስትያን እንደዚህ አይነት ጥያቄ ፈፅመው አይጠይቁም ነበር። ይሄ የመያዣ ጥያቄ ነው።» ከዛ ከጠለ። « ሁለቱንም ነኝ።» የሱ ትውልድ « እኔ አሜሪካዊና ሙስሊም ወይም ሙስሊምና አሜሪካዊ» ነኝ ለማለት አይከብደውም። ከዛም አለ «ማንኛውንም አስቀድመን ብንል የሚያመጣው ለውጥ የለም።»

ክርስቲና በርግማን

ዳኒኤል ሼሽኬቪትዝ

ልደት አበበ