እንደራሴዋ ተገደሉ | ዓለም | DW | 16.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

እንደራሴዋ ተገደሉ

እንደራሴዋ በነበሩበት አካባቢ በተተኮሰዉ ጥይት አንድ የ77 ዓመት አዛዉንትም ቆስለዋል።ፖሊስ ተኩስ ከፍቷል ብሎ የጠረጠረዉን የ52 ዓመት ጎልማሳ መያዙን አስታዉቋል።

የብሪታንያዋ እንደራሴ ጆ ኮክስ ሰሜናዊ ኢንግላንድ ብሪስቶል ዉስጥ በጥይት ተደብድበዉ ተገደለ።የሰራተኛዉ ወይም ሌበር ፓርቲ እንደራሴ የነበሩትን የ41 ዓመቷ እንደራሴ የተገደሉበት ምክንያት በግልፅ አልታወቀም።ይሁንና እንደራሴዋ እጅግ የተከራረዉ ብሪታንያ ከአዉሮጵ ሕብረት አባልነት ትዉጣ አትዉጣ የሚለዉ ፖለቲካዊ ዘመቻ ሰላባ ናቸዉ ብለዉ ታዛቢዎች ይገምታሉ።እንደራሴዋ በነበሩበት አካባቢ በተተኮሰዉ ጥይት አንድ የ77 ዓመት አዛዉንትም ቆስለዋል።ፖሊስ ተኩስ ከፍቷል ብሎ የጠረጠረዉን የ52 ዓመት ጎልማሳ መያዙን አስታዉቋል።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ