እንከን የገጠመዉ የጄኔቫ ጉባኤ | ዓለም | DW | 20.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እንከን የገጠመዉ የጄኔቫ ጉባኤ

በተመ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት የዘር፤ የቀለም፤ የኃይማኖትና ሌሎችንም የጥላቻ ዘመቻዎች ለመቋቋም በጄኔቫ ስዊዘርላንድ በዛሬዉ ዕለት የተጀመረዉ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ከፍተኛ መሰናክል አጋጥሞታል።

default

ባን ጊ ሙን ጉባኤዉ ሳይጀመር

ጉባኤዉ አሁን በጄኔቫ ሲደረግ ሁለተኛዉ ሲሆን የመጀመሪያዉ በአዉሮጳዉያኑ በ2001ዓ,ም ደርበን ደቡብ አፍሪቃ ላይ ተካሂዷል። ይህ ጉባኤም ከዚያ ወዲህ በተጠቀሱት የሰብዓዊ መብቶች ረገድ የተከናወኑ አዎንታዊና አሉታዊ ርምጃዎችን እንደሚገመግም ይጠበቃል። በጄኔቫዉ ጉባኤ እንደማይካፈሉ ካሳወቁት አገራት አንዷ ጀርመን ናት። ጀርመን አቋሟን ትናንት ማምሻዉን ይፋ ስታደርግ የኢራኑ ፕሬዝደንት አህመዲ ነጃድ እስራኤልን የሚያጥላላ ንግግር ማድረጋቸዉ እንደማይቀር ጠቁማ ነዉ። ጀርመን የተመድ አባል ከሆነች ወዲህ ድርጅቱ የጠራዉን ጉባኤ ላይ እንደማትሳተፍ ስትገልፅ ይህ የመጀመሪያ ነዉ።

ድልነሳ ጌታነህ/ይልማ ኃ/ሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ