እንቁጣጣሽ-የ2007 ልዩ ዝግጅት | ኢትዮጵያ | DW | 11.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

እንቁጣጣሽ-የ2007 ልዩ ዝግጅት

እንኳን ከዘመን በሰላም አሸጋገራችሁ አሸጋገረን እንኳን ለአዲሱ 2007 ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። ዶቼ ቬለ የአማርኛዉ አገልግሎት ለመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የጤና የሰላም እና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ይመኛል።

የአዉዳመቱን ዝግጅት ከአዲስ አበባ የፓትርያርኩን መልክት ይዘን፤ በኢትዮጵያ አሮጌዉን ዓመትን ጥሎ ወደ አዲሱ ዓመት የተዛወረዉ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ችግር፤ ክብረ በዓሉ ላይ ያጣለዉን አሉታዊ ገፅታ ዳሰን፤ በአዉሮጳና ና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አዲስ ዓመትን እንዴት እንተቀበሉት? አዲስ ዓመትን በሃገራቸው በድምቀት ያከበሩ ኢትዮጵያውያን ከሃገር ሲወጡ ከትዝታቸው ጋር ነው።ለስራ ወይም ለትምህርት በተጓዙባቸው ሃገራት በዓልን በቀደመው ልክ ማክበር አይሆንላቸውም። የአዲስ ዓመት በዓል ትዝታ ምን ይመስላል? ከአዲስ አበባ ከለንደን ከጀርመን እና ከዩኤስ አሜሪካ ያዘጋጀናቸዉን የአዉዳመት ልዮዝግጅት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic