እናት ባንክ | ኢትዮጵያ | DW | 25.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

እናት ባንክ

አዲስ የተቋቋመ ባንክ ሥም እንጂ የባንኮች ሁሉ እናት ወይም ጠቅላይ ባንክ ለማለት አይደለም ። ይሁንና፣ ከ 720 በሚበልጡ ባለአክሲዮኖች፤ አሁን በእጁ ባለ 120 ሚሊዮን ፣ ቃል በተገባም ሆነ በተፈረመ ስምምነት መሠረት ደግሞ፣

default

260 ሚሊዮን ብር መንቀሳቀሻ ወረት የሚኖረውን አዲሱን ባንክ የተለየ የሚያደርጉት አንዳንድ ነጥቦች አሉ። በቅርቡ ሥራውን የጀመረው አዲሱ ባንክ 64 በመቶ የአክሲዮን ባለድርሻዎች ሴቶች ናቸው። የባንኩ የመጀመሪያ ቅርንጫፍ «ጣይቱ» የሚል ሥያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ ንግሥተ ሳባና አበበች ጎበና የሚሰኙ ቅርንጫፎችም ፣ ባንኩ የሚከፍት መሆኑን አስታውቋል። ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄደው የባንኩ ቅርንጫፎች፤ በኢትዮጵያ ታሪክ አወንታዊ አስተዋጽዖ ባደረጉ ሴቶች ሥም እንደሚሰየሙም ተመልክቷል። ሴቶች ላቅ ያለ የአመራር ኀላፊነት የተሸከሙበት ፣ ከፍ ያለ የሥራ ድርሻም የሚያበረክቱበት ባንክ መክፈት ለምን አስፈለገ?


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic