ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙ ሁሉ ያሻቸውን በማኅበራዊ ድረ ገፆች ማሠራጨት በሚችሉበት በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲህ አይነቱን ዕድል ገድቧል። በኢትዮጵያ ቲክ ቶክ፣ ኢንስታግራም ወይም ዩቲዩብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን የተከለከሉት የተቃዋሚ አባላት ብቻ አይደሉም።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ዘገባው ከ25ሺ በላይ ሰዎች ከሱዳን በ3 ክልሎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አመልክተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከ6ሺ በላይ ሰዎች የሚሆኑት በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አል-ማሀል በተባለ ስፍራ እና በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ የገቡ ናቸው፡
በትግራይ ተማርከው ከነበሩ ወታደሮች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት ያለ ደመወዝ በአስቸጋሪ ሁኔታ በጦር ሰፈር ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ባለማዕረግ ወታደሮች በመከላከያ ሠራዊት "ከህወሓት ተባብራችኋል" የሚል ክስ ከተቀሩት ምርኮኞች መለየታቸውን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉዳያቸውን እየተከታተለ ይገኛል።