እስክንድር ነጋ ኢሕአዴግ ባሳለፈው ውሳኔ ይፈታ ይሆን?  | ኢትዮጵያ | DW | 09.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

እስክንድር ነጋ ኢሕአዴግ ባሳለፈው ውሳኔ ይፈታ ይሆን? 

ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በገና ዋዜማ ባለቤቷ፣ የልጇ አባት እስክንድር ነጋ ይፈታል ብላ ተስፋ አድርጋ ነበር። ለባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል እስክንድር ይፈታ ይሆናል የሚል ተስፋ የሰጣት ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሹማምንት የሰጡት መግለጫ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:24

የኢሕአዴግ ሊቃነ-መናብርት እስረኛ እንፈታለን ካሉ ቀናት ተቆጠሩ

ጋዜጠኛው ከሽብር ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሕቡዕ ግንኙነት በማድረግ፣ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ስብሰባ በማድረግ፣ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በመስማማት፣ ቀስቃሽ ፅሁፎችን በመፃፍ እና በማሰራጨት የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን የመተላለፍ ክስ ተመስርቶበት ነበር የታሰረው። ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18 አመታት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። ለባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል  እስክንድር ይፈታ ይሆናል የሚል ተስፋ የሰጣት ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሹማምንት የሰጡት መግለጫ ነው።

በመግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ "በፈጸሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸውም ወይም ደግሞ በአቃቤ- ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው እና ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ሆነ ግለሰቦች" ሊፈቱ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ አመራሮች እና ግለሰቦች ያሏቸው እስረኞች የሚፈቱት «ክሳቸው ተቋርጦ እንደዚሁም ደግሞ የምሕረት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ምሕረት ተደርጎላቸው» እንደሆነም አክለዋል።

ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እንደምትለው እስክንድር "አንዳንዶች" ከተባሉት ጎራ ተመድቦ ይፈታ ይሆናል የሚል ተስፋ አሳድራ ነበር። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ አነጋግሯታል።

 
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ 
አርያም ተክሌ
 

Audios and videos on the topic