እስከ ማምሻ ድረስ የተፈታ የለም። | ኢትዮጵያ | DW | 09.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

እስከ ማምሻ ድረስ የተፈታ የለም።

በተለይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌ ዛሬ እንዲፈርሙ ተሰጣቸው የተባለ ፎርም ይዘት ውዝግብ አስነስቶ መግባባት ላይ አለመድረሳቸውን ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:01

እስከ ማምሻ የተፈታ እንደሌለ ዘጋቢያችን ገልጾልናል።

በይቅርታ እንዲፈቱ ተወስኖላቸዋል ከተባሉት ታራሚ እና ተጠርጣሪዎች መካከል እስከ ዛሬ ማምሻ ድረስ የተፈታ አለመኖሩን ወደ ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የተጓዘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ገልጾልናል። መንግሥት እስረኞች እንዲፈቱ ወስኗል ከተባለ በኋላ ከዛሬ ጠዋት አንስቶ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነዉ።  በተለይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌ ዛሬ እንዲፈርሙ ተሰጣቸው የተባለ ፎርም ይዘት ውዝግብ አስነስቶ  መግባባት ላይ አለመድረሳቸው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል። አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እስረኞችን በመፍታት ሂደት ተነሱ በተባሉ ውዝግቦች ላይ አስተያየት እየሰጡ ነው። ይህን እና ከእስረኞች መለቀቅ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ወደ ቅሊንጦ ሄዶ የነበረውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን በስልክ አነጋግረነዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic