እስራኤል 40 ሺህ ተገን ጠያቂዎችን ከሀገሯ ልታስወጣ ነው | ዓለም | DW | 21.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

እስራኤል 40 ሺህ ተገን ጠያቂዎችን ከሀገሯ ልታስወጣ ነው

የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ 40,000 አፍሪቃውያን ተገን ጠያቂዎችን ከሀገራቸው ለማስወጣት ዓለም አቀፍ ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ከትናንት በስቲያ እሁድ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለስምምነቱ ዝርዝር ነገር ባይናገሩም "እጅጉን ጠቃሚ ነው" ብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:16

የእስራኤል ርምጃ ኤርትራውያን ስደተኞችን ይመለከታል

ከእስራኤል የሚባረሩት ተገን ፈላጊዎች ያለፈቃዳቸው እንደሆነ በዘገባዎች ተገልጿል። ከጎርጎሮሳዊው 2000 የመጀመሪያ አመታት ጀምሪሮ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን በግብፅ በኩል ወደ እስራኤል ቢገቡም በሀገሪቱ ግን ተቀባይነት አላገኙም። ስደተኞቹ በእስራኤላውያን ዘንድ "ሰርጎ ገቦች" የሚል ስም እንደተሰጣቸው ዘገባዎች አመልክተዋል።  ሐሬትዝ የተባለው የእስራኤል ዕለታዊ ጋዜጣ ኔታንያሁ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ስምምነት ደርሰዋል ሲል ባለፈው ወር ዘግቦ ነበር። እየሩሳሌም ከሚገኘው ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንን ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ዜናነህ መኮንን

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ 
   

Audios and videos on the topic