እስራኤል ጠ/ም በምስራቅ አፍሪቃ | ኢትዮጵያ | DW | 07.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

እስራኤል ጠ/ም በምስራቅ አፍሪቃ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከትናንት አንስቶ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አስቀድሞ ጉብኝት ባደረጉባቸው በዩጋንዳ፣ በኬኒያ እና በሩዋንዳ እስራኤል ከአፍሪቃ የተሻለ ወዳጅ የላትም ሲሉ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:15

እስራኤል በአፍሪቃ

ግን እስራኤል ያሉት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎችም አፍሪቃውያን የእስራኤል የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያሳስባቸዋል። እስራኤል ወዳጅነቱን ለማጥበቅ የፈለገችው የፖለቲካ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ነዉ ሲሉም ይተቻሉ።

በእስራኤል ወደ 45,000 የአፍርቃ ስድተኞች እንደምገኙ፣ ከዝህም 92 በመቶዉ ኤርትራዊያኖች እና ሱዳኖች መሆናቸዉ ዘገባዎች ያሳያሉ።

ይሁን እንጅ የእስራኤል መንግስት ባለፉት ሁለት ዓመታት ዉስጥ ወደ 3000 ኤርትራዊያን እና ሱዳናዊያን ስድተኞችን በሚስጥር ወደ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ መመለሱ ተዘግበዋል። በዩጋንዳ እና በሩዋንዳ ያደረጉት ጉብኝት ይህን ስምምነት ለማጠናከር ነው ብለው የሚተቹም አልጠፉም።


በዝህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ ደረ ገፅ ላይ አዋያይተን ነበር። ከአስተያየት ሰጨዎችም የጠቅላይ ምንስትሩ ጉቢኝት የዲፕሎማሲ ግንኑኝነቱን ለማጠናከር ያለመ እንደመሆኑ በፖለቲካም፣ በእኮኖሚም፣ በወታደራዊ እና በድህንነት ጉዳዮች አብረው እንድሰሩ ያደርጋል ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ጉብኝታቸዉ በእስራኤል ዉስጥ በአፍሪቃ ስደተኞች ላይ ለሚፈፀመዉን በደል የሚያመጣ ለውጥ አይኖርም ስሉ አስተያየታቸዉን ሰተዋል።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic