እስራኤል በሊባኖስ የከፈተችው ጦርነትና የኢራን የሚሳይል ጥቃት ወዴት ያመራ ይሆን?
ሐሙስ፣ መስከረም 23 2017እስራኤል በሊባኖስ የከፈተችው ጦርነትና የኢራን የሚሳይል ጥቃት
እስራኤል፤ በራሷና ምራባውያን መንግስታት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሃማስ ባለፈው አመት መስከረም ወር በሰላማዊ ዘጎቿ ላይ ያደርሰውን ግድያና እገታ ተክትሎ፤ በጋዛ የክፍተቸውን ጦርነት በማስፋት ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በሊባኖስ ሌላ የጦርነት ግምባር ከፍታለች። በሊባኖስ የሚገኘውና በኢራን ይደገፋል የሚባለው እስላማዊ ድርጅት ሂዝቦላ፤ እስራኤል በሀማስ ላይ የክፍተችውን ጦርነት በማውገዝና እየደረሰ ያለውን ውድመት በመቃወም፤ ከደቡብ ሊባኖስ በኩል በእስራኤል ላይ ጥቃት ሲያደርስ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህንን ሀይል ለማስወገድና ከቡድኑ የሚደርስባትን ጥቃት ለመከላከል በሚል በተለይ ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በቡድኑ ላይ ጦርነት ከፍታ ቆይታለች።
መካከለኛው ምስራቅ አዲሱ የጦር አውድማ ወይስ ?
ካአስር ቀናት በፊት ፈንጂ በተቀበረላቸው የመገናኛ መሳሪያዎች አማካይነት በሂዝቦላ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፤ ባለፈው ዓርብና ከዚያም ወዲህ ደግሞ፤ እስራኤል ደቡብ ሊባኖስና ቤይሩት ጭምር ባደረሰችው ጥቃት፤ የቡድኑን መሪና በርክታ የአመራር አባላቱን አስወግዳለች።
የዓለማቀፉ ማህብረሰብ የተኩስ ማቆም ጥሪና የእስራኤል ምላሽ
በጋዛ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ ሲጠይቅ የቆየው አለማቅፉ ማህብረሰብ፤ በሊባኖስ ግምባርም የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዴደርግ ጥሪ ቢያደርግም፤ እራኤል ግን ዘመቻውን በምድርም ጭምር እንደምትገፋበት ነው የገለጸችው። በዚህ መሀል ኢራን ትናንት ከሰአት በኋላ በሊባኖስና ጋዛ የተፈጸሙትን ግድያዎች ለመበቀል በሚል ከሁለት መቶ በላይ ሚሳይሎችን በኢስራኤል ሰማይ ላይ በማዝነብ መላ አገሪቱን የጦርነት አውድማ አድርጋት የንበር ሲሆን ፤ መላ ህዝቧም ለተወሰኑ ሰአታትም ቢሆን በምሺግ እንዲቆይ ተገዶ ቆይቷል። እስራኤል ከኢራን የተሰነዘረው ጥቃት አምና ያአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች። ኢራን በበኩሏ ጥቃቱ ለግዜው የቆመ መሆኑን በመግለጽ የስራኤል ጥቃት ካልቆመ ግን እርምጃው አይሎ እንደሚቀጥል ገልጻለች።
ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ አሁንም ችግር ላይ ናቸው
የኢራን ጥቃትና የእስራኤል ዛቻ የፈጠረው ስጋት
አንድ አመት የሚሆነው በጋዛ የተክፈተው ጦርነት ከ40 ሺ በላይ ፍልስቴሞችን መግደሉና በብዙ ሺ የሚቆጠሩትን ማፈናቀሉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከሁለቱም ወገኖች የሚሰሙት መግለጫዎችና ወታደራዊ እርምጃዎች በአካባቢው ያለውን ግጭትና ጦርነት የበለጠ እንዳያሰፋው አስግቷል።
የዓለማቀፉ ማህብረሰብ ውግዘትና መግለጫዎች
አሜሪካ የኢራንን ጥቃት አውግዛ ከእስራኤል ጎን የምትቆም መሆኑን እራሳቸው ፕሬዝዳንት ባይደን አረጋግጠዋል። የብርታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስተር ሚስተር ኬይር ስታርመርም እንደዚሁ ከእስራኤል ጎን እንደሚሰለፉ ገልጸዋል። ሌሎችም ፈረንሳይና ሌሎች አገሮች፤ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ፤ ኢራን በእስራኤል ላይ ያደርሰችውን የሚሳይል ጥቃት አውግዘዋል። የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በዚሁ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ዛሬ እንደሚመክርም ታውቋል።
በኢስራኤል ላይ እንዴት ተጽኖ መፍጠር ይቻላል?
አብዛኛዎቹ ምራባውያና አገራት አሜሪካም ጭምር እስራኤል በሊባኖስ በኩል የከፍተቸውን ጦርነት እንደሚቃወሙና ባጋዛም የትኩስ ማቆም እንደደረግ እንደሚፈልጉ ነው የሚገለጸው።ወቅቱ የምርጫ ወቅት መሆኑ የአሜሪካ ፖለቲከኖች በኣስራኤል ላይ ደፍረው እርምጃ እንዳይወስዱ አድርጓቸዋል የሚሉም አሉ።
በፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ወቅት ዲፕሎማት የነበሩት ሚስተር ብሬት ብሩን፤ በአሁኑ ወቅት ከአሜርካ በኩል በእስራኤል የመስማት ችግር አለ ነው የሚሉት። እንደእሳቸው አስተያየት ከሆነ፤ አሜሪክና አጋሮቿ ኢስራኤል የተኩስ ማቆሙን ጥያቄ እንድትቀበል ለማድረግ የሚያስችሉ በርክታ ዘዴዎች አሏቸው፤ “ አንዱ የቀን ገደብ ቆርጦ ማስቀመጥ ነው። የተወሰኑ የጦር መሳሪያዎች ላይም ማዕቀብ መጣል ይቻላል” በማለት አሜሪካ ካውሮፓ አጋሮቿ ጋር ሆና ሚስተር ናታኒያሁን አለም በተኩስ ማቆም ጥያቄው ላይ አንድ ላይ የቆመ መሆኑን በማስገንዘብ ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲመጡ ማደረግ እንደሚቻል አስታውቀዋል
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ