እስራኤልና ፍልስጤም የሰላም ዉይይት | ዓለም | DW | 13.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እስራኤልና ፍልስጤም የሰላም ዉይይት

እስራኤልና ፍልስጤም የጀመሩት ቀጥተኛ የሰላም ድርድር ነገ ረቡዕ እንደሚቀጥል የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010 ዓ,ም ተቋርጦ የነበረዉ የእስራኤል እና የፍልስጤም የሰላም ድርድር፤ አሜሪካን ለወራት ካደረገችዉ ጥረት በኋላ፤ የሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎች ከሳምንት በፊት ዋሽንግተን ላይ፤ ለዉይይት መገናኘታቸዉ ይታወቃል። የሰላም ዉይይቱ የድንበር ማካለልን ጨምሮ የኢየሩሳሌም እና የተመዘገቡ 5,3 ሚሊዮን ፍልስጢማዉያን ስደተኞች የወደፊት እጣ ፈንታ ፤ እንዲሁም የእስራኤል የፀጥታ ሁኔታ ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል። እስራኤል ከእስር የምትለቃቸዉን የ 26 ፍልስጤማዉያን እስረኞች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል ። በእየሩሳሌም የሚገኘዉን ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን ስለሰላም ዉይይቱ በስልክ ጠይቄዉ ነበር።


ዜናነህ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic