እስራኤልና ጥብቁ የስደተኞች አመራር ዘይቤዋ | ዓለም | DW | 04.06.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እስራኤልና ጥብቁ የስደተኞች አመራር ዘይቤዋ

60,000 አፍሪቃውያን ስደተኞች የሚገኙባት እሥራኤል ፤ ከእንግዲህ ሌሎች እንዳይገቡ፤ የገቡትም ከመጡባቸው አገሮች ጋር በሚደረግ ስምምነት እንዲመለሱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆንዋ ከመነገሩም ሌላ፤ ህገ ወጥ በሚባሉት ስደተኞች ላይ ጥብቅ እርምጃ ለመወሰድ ተነሳስታለች።

አንዳንድ የመንግሥት አባላት በሚሰነዝሯቸው የስደተኞችን መብዛት የማጥላላት ንግግርም ሳቢያ፤ በስደተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ቀጥሏል። ዛሬ ጧት፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ፣ 18 የኤርትራ ተወላጆች በሚገኙበት በአንድ አሮጌ ባለ 2 ፎቅ ህንጻ ላይ ሆን ተብሎ በተወሰደ የማቃጠል እርምጃ 4 ኤርትራውያን የመቁሰልና በጢስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሀኪም ቤት መወሰዳቸው ተነግሯል። እሥራኤል ለምንድን ነው በስደተኞች ላይ ጠጣር እርምጃ የምትወስደው? ፤ በዚያው በእሥራኤል ፣ የመንግሥት ያልሆነውን ፤ የአፍሪቃ ስደተኞች የዕድገት ማዕከል የተሰኘውን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ባዩን ወደ እስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬአቸው ነበር።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 04.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/157sn
 • ቀን 04.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/157sn