እስራኤልና በፍልስጤማውያን ግዛት የቀጠለችው የሰፈራ ግንባታዋ | ዓለም | DW | 06.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እስራኤልና በፍልስጤማውያን ግዛት የቀጠለችው የሰፈራ ግንባታዋ

እስራኤል በያዘችው የምዕራባዊ ዳርቻ የሰፈራ ቦታ ግንባታዋን ቀጠለች።

default

የሰፈራ ቦታ በኢየሩሳሌም

«ሰላም አሁን» የሚባለው ድርጅት ባወጣው ዘገባ መሰረት፡ ምንም እንኳን እሥራኤል፣ ግንባታውን እንድታቋርጥ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፡ በተለይ ከዩኤስ አሜሪካ ተጽዕኖ ቢያርፍባትም ይህን ችላ በማለት ስምንት መቶ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ትገኛለች። ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በሰላሳ አራት ቦታዎች የሰፈራ ግንባታው ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል። ይህም በፍልስጤማውያን እና በእስራኤል መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት እንዳያደናቅፍ እጅግ ነው ያሠጋው።

ዜናነህ መኮንን/አርያም ተክሌ/ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic