እስላማዊ ትብብር ድርጅት እና ሶርያ | ዓለም | DW | 14.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

እስላማዊ ትብብር ድርጅት እና ሶርያ

መቀመጫውን ሳኡዲ አረቢያ ያደረገው እስላማዊ ትብብር ድርጅት የተሰኘው ግዙፍ ተቋም ሶሪያን ከአባልነቷ ለማገድ የሚያስችል ውሳኔ ማርቀቁ ተገለፀ።

ይህ በሳዑዲ አረቢያ ንጉስ አብደላ ቢን አብደል አዚዝ አሳሳቢነት በአስቸኳይ የተጠራው እና 57 አባል ሀገራትን ያቀፈው የዓለም አቀፍ የሙስሊም ሀገራት ትብብር ጉባኤ ትናንት ማምሻውን ነበር በመካ የጀመረው። ጉባኤው ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የኢራኑ ፕሬዚዳንት አህመዲን ነጃድን ጨምሮ በርካታ የሙስሊም እና የአረብ ሐገራት መራሄ-መንግስታት ትናትና እና ከትናት በስተያ መካ መግባታቸውም ተዘግቧል። የሳዑዲ አረቢያ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ ጉባኤውን ቃኝቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።


ነቢዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic