እርዳታ ከሳውዲ ለተባረሩ ኢትዮጵያውያን | ኢትዮጵያ | DW | 29.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

እርዳታ ከሳውዲ ለተባረሩ ኢትዮጵያውያን

ከሳውዲ አረቢያ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ አሜሪካ ውስጥ በኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ማህበር 2 ተኛ የገንዘብ ድጋፉን አበረከተ ።

ማህበሩ ለኢትዮጵያውያን እርዳታ የሚውል 32 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ተቋም በምህፃሩ IOM ለግሷል። በኢትዮጵያውያኑ ጥያቄ መሠረት ገንዘቡ በተለይ ከሳውዲ አረቢያ ወደ የመን ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን መርጃ እንደሚውል የIOM የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ማርያ ሞንሮ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic