እሥራኤልና የአፍሪቃውያን ስደተኞች ዕጣ | አፍሪቃ | DW | 25.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

እሥራኤልና የአፍሪቃውያን ስደተኞች ዕጣ

የእሥራኤል ሚንስትሮች ም/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ናቸው ያላቸውን አፍሪቃውያን ስደተኞች፤ በግዴታ እንዲመለሱ ማድረግ የሚቻልባቸውን የእርምጃ ዓይነቶች ትናንት ማጽደቁ ተነግሯል። እሥራኤል የገቡ 60,000 ያህል ስደተኞች ወደ መጡበት

እንዲመለሱ ለማስገደድ የእሥራኤል መንግሥት፣ የተለያዩ የስደተኞችን እንቅሥቃሴ የሚገቱና ተስፋ የሚያስቆርጡ እርምጃዎችንም በመውሰድ ላይ ነው። ስደተኞቹ አግባብ ያለው መፍትኄ እንዲያገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምን ማድረግ ይችላሉ? ተክሌ የኋላ ፣ በአሥራኤል የአፍሪቃውያን ስደተኞችን የልማት ማዕከል ሥራ አስኪጅ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ድምፅ እንዲሰጥበት ዛሬ ለፓርላማ የሚቀርበው አዲሱ የስደተኞችን ዕጣ ፈንታ የሚመለከተው ደንብ ፣ አምና የወጣውን ፤ ስደተኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እስከ 3 ዓመት እንዲታሠሩ የሚያዘውን የህግ አንቀጽ የሚሽር ነው ። ይህም የሆነው የሥራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው መስከረም የመጀመሪያውን 3 ዓመት የሚለውን ደንብ ሽሮ ፣ በአንድ ዓመት እንዲገደብ ብይን በመስጠቱ ነው። ያን ያህል ውጣ -ውረድ ለምን አስፈለገ ?ስደተኞቹ ተገልለው በረሃ ላይ በአንድ መጠለያም ሆነ ማጎሪያ ቦታ እንዲቀመጡ መወሰኑስ ለምን ይሆን?በእሥራኤል የአፍሪቃውያን ስደተኞች የልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ባዩ---

የእሥራኤል መንግሥት ወደ ግዛቱ ፣ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ገቡ ያላቸውን ሰዎች፤ በተደጋጋሚ ለሀገሪቱ ፀጥታ አስጊዎች ናቸው ነበረ ያለው። እንዲያውም ፤ በአገላለጹ ሠርጎ ገብ (infltrators)የሚለውን ቃል ነው የሚጠቀመው። የተባሉት ሰዎች እስከምን ድረስ በእሥራኤል ፀጥታ ላይ አደጋ ደቅነው ይሆን፦ በጥናት የሚታወቅ ነገር ይኖር ይሆን!

እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙት ስደተኞች መካከል በዛ ያሉት ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ናቸው ፤ ኢትዮጵያውያንም አሉ። አሁን እንደተባለው የእሥራኤል መንግሥት ስደተኞች አገር ለቀው እንዲወጡለት ነው አጥብቆ የሚሻውና ትኩረትም ያደረገው።

አንዱ እርምጃው፤ ለመቋቋሚያ የሚሰጠውን ገንዘብ ከ 1500 ወደ 3,500 ዶላር ከፍ ማድረግ ነው። 10 ሺ ያህል ስደተኞችን ተቀብሎ ለሚያስተናግድለት ከ 2 የአፍሪቃ አገሮች ለአንደኛው የጦር መሣሪያና ሌላም ሌላ እርዳታ ለማቅረብ ሐሳብ እንዳለው የተገለጠበት ጊዜም ነበረ። በስዑዲ ዐረቢያ የተፈጸመው ዓይነት እርምጃ በእሥራኤል የማይታሰብ ነው ቢባልም ስደተኞቹ፣ ከጭንቀት የሚገላግላቸው መላ አላገኙም ፤ አልተገኘላቸውም።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic