እልፍ ሲሉ እልፍ--- | ኢትዮጵያ | DW | 01.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

እልፍ ሲሉ እልፍ---

ይህችው መከረኛ ኢትዮጵያዊት የደረሰባት ግፍ፤ አሁን ጎልቶ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገለጥ እንጂ በብዙ የዐረብ አገሮች ፤ ኢትዮጵያውያት ተመሳሳይ በደል ይፈጸምባቸዋል።

default

በሳምንቱ መግቢያ ገደማ ላይ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ወንድ ልጅ፤ ሃኒባል ጋዳፊ ቤት ውስጥ፤ ልጅ አሳዳጊ ሆና ትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት፤ የደረሰባትን ዘግናኝ በደል፤ CNN በሚል ምህጻር የታወቀው የቴሌቭዥን ድርጅት ማጋለጡ የሚታወስ ነው። ይህችው መከረኛ ኢትዮጵያዊት የደረሰባት ግፍ፤ አሁን ጎልቶ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገለጥ እንጂ በብዙ የዐረብ አገሮች ፤ ኢትዮጵያውያት ተመሳሳይ በደል ይፈጸምባቸዋል። «እልፍ ሲሉ እልፍ ሳይሆን መከራ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ስንቶቹ ናቸው የሚያስቡት? የችግሮቹን፤ የፈተናዎችን ዓይነቶች ፤ በሊቢያ ግፍ ከተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት ታሪክ በመነሳት ፤ ነቢዩ ሲራክ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች