እልባት ያልተገኘለት የኮት ዲ ቯር ውዝግብ | ኢትዮጵያ | DW | 09.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

እልባት ያልተገኘለት የኮት ዲ ቯር ውዝግብ

ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ውዝግብ የቀጠለባት ኮት ዲቯር በዐረቡ ዓለም በመካሄድ ላይ ባለው የህዝብ ዓመጽ የተነሳ የመረሳት ዕጣ ገጠማት።

default

በፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተሸፉት የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሎውሮ ባግቦ አሁንም ስልጣናቸውን ለአሸናፊው አላሳን ዋታራ አላስረክብም እንዳሉ ነው። በባግቦ ወታደሮች እና በዋታራ ደጋፊዎች መካከል ግጭቱ ቀጥሎዋል። ውዝግቡ የሚያበቃበትን ዘዴ እንዲያፈላልግ የአፍሪቃ ህብረት የሰየመው አምስት የአፍሪቃ ሀገሮች ፕሬዚደንቶችን ያቀፈው የሽምጋዮች ቡድን በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከሁለቱ ተቀናቃኞች ጋ ለመምከር ዕቅድ ቢኖረውም፡ ባግቦ በምክክሩ ላይ እንደማይገኙ ከወዲሁ አስታውቀዋል።

Elfenbeinküste Thabo Mbeki Besuch

ብዙ የዋታራ ደጋፊዎች በሚኖሩበት በሰሜን አቢዣ ጎስቋላው የአቦቦ ሰፈር በመቶ የሚቆጠሩ ዋታራ የሚደግፉ ሴቶች አዶ እያሉ ለሚጠሩዋቸው ዋታራ ድጋፋቸውን ለመስጠት ባለፈው ሳምንት አደባባይ በወጡበት ጊዜ ያሰሙት መፈክር ነበር። የህዝብ ድምጽ ሰርቀዋል ያሉዋቸው ባግቦ ስልጣኑን ዓለም አቀፍ እውቅና ላገኙት ዋታራ እንዲያስረክቡ ነው የጠየቁት በዚሁ ጊዜ የባግቦ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ስድስት ሴቶች ሲገድሉ በርካቶችን አቁስለዋል። አንድ ያይን ምስክር ስለ ሁኔታው ሲናገሩ፡

«ሴቶቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ነበር የወጡት። የጦር መሳሪያ አልታጠቁም። በድንገት የባግቦ ታንኮች መጥተው በህዝብ ላይ ተኩስ ከፈቱ። »

ይህንን ያይን ምስክር ተገባ አሶሽየትድ ፕሬስ ያወጣው ቪድዮ የባግቦ ደጋፊዎች እና ታንኮቻቸውን ቢያሳይም፡ ባግቦ ዘገባውን ሀሰት ብለው በማስተባበል፡ ለግድያው የአቦቦ አሸባሪዎች እንደሆኑ ነው ያስታወቁት። እንዲያውም በሀገሪቱ ያለው የተመድ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ለአሴቶቹ ግድያ ተጠያቂ የሆኑ አሸባሪዎችን ወደሀገሪቱ እያስገባ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። በኮትዲቯር የተመድ ተልዕኮ ቃል አቀባይ ሀማዱን ቱሬ አሳዛኝ ብለውታል።

«በአቦቦ ሰብዓዊ ርዳታ የሚያቀርብ፡ አስከሬኖችን የሚሰበስብ ቡድን የለንም፡ ይህ ነው ችግሩ። ለዚህም ነው በአቦቦ የተኩስ አቁም ደምብ እንዲወጣ የጠየቅነው። የሰብዓዊ ርዳታ አቅራቢዎች ቢያንስ ሟቾቹ ተገቢው ቀብር እንዲደረግላቸው ሊረዱ ይችሉ ነበር። »

በተቀናቃኞቹ ወገኖች በቀጠለው ግጭት የተነሳ ከአቦቦ ብቻ ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጥ ህዝብ መሸሹን ሙሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ባልደረባ ሀዋ ገልጸዋል።

Elfenbeinküste Unruhen in Abidjan Flüchtling

«ባግቦ እንዲወርዱ ከብዙ ጊዜ ወዲህ እየጠየቅን ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን እንደሚጠብቅ አላውቅም። ምናልባት ብዙ ሰው እንዲሞት እና የባሰ ጭፍጨፋ እንዲካዴድ ይህን የሚጠብቀው። በየቀኑ የሚታየው ስዕል አስከፊ ነው። እና እኛ ተቃውሞአችንን እንቀጥላለን።»

ሁኔታው በርግጥ አሳሳቢ መሆኑን የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አድሪያን ኤድዋርድስ ገልጸዋል።

ባለፈው ህዳር ወር ከተካሄደው ምርጫ በኋላ እጅግ ብዙ ህዝብ ድንበር ተሻግሮ ላይቤሪያ ሲሄድ ተመልክተናል። ከነዚሁ መካከል ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የያዙ ሴቶች ነበሩ። አሁን መላ ቤተሰብ ሲሰደድ ነው የምናየው ያለነው። ይህም የህዝቡ መፈናቀል ለብዙ ጊዜ ሊቆይል እንደሚችል ነው የሚጠቁመው።

አንድ ተፈናቃይ ይህን አባባል አረጋግጦዋል።

«በኮት ዲቯር ሁኔታው ካልተረጋጋ እኔ ወደዚያ አልመለስም።»

የባግቦ ጦር ኃይላት እና የዋታራ ታማኝ የሆኑት በሰሜን የሀገሪቱ ከፊል የሚንቀሳቀሰው የፎርስ ኑቬል ዓማጽያን ከውጭ በሚያገኙት ድጋፍ ራሳቸውን በማስታጠቅ ላይ እንደሆኑ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። ባግቦ ምንም እንኳን በኮካው ንግድ ላይ ዕገዳ ቢያርፍም፡ ገንዘብ አላጠራቸውም።

ይህ እና የኃይሉ ተግባር መባባስ ሀገሪቱን ።

Elfenbeinküste Ausschreitungen

እአአ በ 2002ዓም የታየውን እና ሀገሪቱን ለሁለት የከፋፈለውን ዓይነት የርስበርስ ጦርነት ሊያስከትል እንደሚያችል የተመድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እያስጠነቀቁ ነው። የፎርስ ኑቬል ዓማጽያን ባለፈው ሰኞ ከመፍቀሬ ባግቦ ዣይላት ጋ ባካሄዱት ውጊያ በምዕራባዊው የሀገሪቱ ከፊል ሶስተኛ ከተማ መያዛቸውን አመልክተዋል። መላው ዓለም ትኩረቱን በሊቢያ ላይ ባሳረፈበት ባሁኑ ጊዜ በኮት ዲቯር ደም መፋሰሱ ቀጥሎዋል። ዛሬ በአቦቦ ቆየት ብሎም በመላይቱ ሀገር እንዳይዛመት አስግቶዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ፡ የአፍሪቃ ህብረት ባግቦ ስልጣናቸውን ለአላሳን ዋታራ እንዲያስረክቡ ያደረገው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ አምስት የአፍሪቃ ሀገሮች ፕሬዚደንቶችን ያቀፈው የሽምጋዮች ቡድን ውዝግቡ የሚያበቃበትን ዘዴ እንዲያፈላልግ ሰይሞዋል። ይኸው ቡድን በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከሁለቱ ተቀናቃኞች ጋ ምክክር ለማካሄድ ያቀደ ሲሆን፡ በባግቦ አንጻር በሰሜናዊ አቢዣ የሚገኙበት ሆቴል በባግቦ ኃይላት የተከበባቸው ዋታራ በዚሁ ምክር ላይ እንደሚካፈሉ አስታውቀዋል።

አሌግዛንደር ገብል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ